የሕያዋኑም መልክ የሚነድድ የእሳት ፍም ይመስል ነበር፥ በሕያዋኑም መካከል የሚነድድ ችቦ የሚመስል ወዲህና ወዲያ ይዘዋወር ነበር፥ እሳቱም ብርሃን ነበረው፥ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር።
ሕዝቅኤል 10:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኪሩቤል መካከል አንድ ኪሩብ እጁን በኪሩቤል መካከል ወዳለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ ወሰደ፥ በፍታ በለበሰው ሰው እጅም አኖረው፥ እርሱም ይዞ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኪሩቤልም አንዱ በመካከላቸው ወዳለው እሳት እጁን ዘርግቶ ጥቂት ወሰደ፤ በፍታ በለበሰው ሰው እጅ ላይ አኖረው፤ እርሱም ይዞ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኪሩቤልም አንዱ በመካከላቸው ባለው እሳት ውስጥ እጁን ሰድዶ ጥቂት ፍሞች አነሣና በፍታ በለበሰው ሰው እጅ ላይ አኖረው፤ ሰውየውም ፍሙን ይዞ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኪሩቤል መካከልም አንዱ ኪሩብ እጁን በኪሩቤል መካከል ወደ አለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ እሳት ወሰደ፤ የተቀደሰ በፍታም በለበሰው ሰው እጅ አኖረው፤ እርሱም ይዞ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኪሩብም ከኪሩቤል መካከል እጁን በኪሩቤል መካከል ወዳለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ ወሰደ፥ በፍታም በለበሰው ሰው እጅ አኖረው፥ እርሱም ይዞ ወጣ። |
የሕያዋኑም መልክ የሚነድድ የእሳት ፍም ይመስል ነበር፥ በሕያዋኑም መካከል የሚነድድ ችቦ የሚመስል ወዲህና ወዲያ ይዘዋወር ነበር፥ እሳቱም ብርሃን ነበረው፥ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር።
በፍታ የለበሰውን ሰው ሲያዘው፦ ከኪሩቤል መካከል ከመንኰራኵሮች መካከል እሳት ውሰድ አለው፥ እርሱም ገብቶ በአንድ መንኰራኵር አጠገብ ቆመ።