La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 34:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“የቂጣውን በዓል ጠብቀው፤ በአቢብ ወር ከግብጽ ወጥተሃልና በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“የቂጣን በዓል አክብር። እንዳዘዝሁህም ለሰባት ቀን ቂጣ ብላ፤ ይህንም በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር አድርግ፤ በዚያ ወር ከግብጽ ወጥተሃልና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ከግብጽ የወጣችሁት በአቢብ ወር ስለ ሆነ የቂጣን በዓል በመጠበቅ በየዓመቱ አክብሩ፤ እንዳዘዝኳችሁ በአቢብ ወር እስከ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“የቂ​ጣ​ውን በዓል ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለህ። በሚ​ያ​ዝያ ወር ከግ​ብፅ ወጥ​ተ​ሃ​ልና በታ​ዘ​ዘው ዘመን በሚ​ያ​ዝያ ወር እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የቂጣውን በዓል ትጠብቀዋለህ። በአቢብ ወር ከግብፅ ወጥተሃልና በታዘዘው ዘመን በአቢብ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ብላ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 34:18
15 Referencias Cruzadas  

“ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ፤ ከዓመቱ ወሮችም የመጀመሪያ ይሁናችሁ።


ከግብጽ ምድር ስላወጣቸው ለጌታ የተጠበቀች ሌሊት ናት፤ ይህች ሌሊት በእስራኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ በትውልዳቸው ሁሉ ለጌታ የተጠበቀች ናት።


ሙሴም ሕዝቡን አለ፦ ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፥ ጌታ ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።


እናንተ ዛሬ በአቢብ ወር ወጥታችኋል።


“በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓልን ታደርግልኛለህ።


የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በተመደበው በአቢብ ወር ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ እንዳዘዝሁህ ትበላለህ፤ በዚህ ወር ከግብጽ ምድር ወጥታችኋልና፥ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ።


በዚህም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን ለጌታ የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን እርሾ ያልነካው የቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ።


“በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን የጌታ ፋሲካ ነው።


ከዚህም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ ሰባት ቀን እርሾ ያልነካው ቂጣ ይበላል።


የፋሲካና የቂጣ በዓል ሊከበር ሁለት ቀን ሲቀረው፥ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ኢየሱስን የሚይዙበትና የሚገድሉበትን ዘዴ ይፈልጉ ነበር።


ፋሲካም ተብሎ የሚጠራው የቂጣ በዓል ቀረበ።


አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ ጴጥሮስን ደግሞ ያዘው። የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ።