አቢሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ አለው፦ “ይህ ያደረግህብን ምንድነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት ያመጣህብን ምን ብንበድልህ ነው? ፈጽሞ የማይገባ ነገር በእኔ ፈጸምክብኝ።”
ዘፀአት 32:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም አሮንን፦ “ይህንን ታላቅ ኃጢአት ታመጣበት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደረገህ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም አሮንን፣ “ወደዚህ አስከፊ ኀጢአት ትመራቸው ዘንድ እነዚህ ሕዝብ ምን አደረጉህ?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንንም “ከቶ ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ነው ይህን የመሰለ አስከፊ ኃጢአት እንዲሠራ ያደረግኸው?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም አሮንን፥ “ይህን ታላቅ ኀጢአት ታመጣበት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደረገህ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም አሮንን፦ ይህን ታላቅ ኃጢአት ታመጣበት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደረገህ? አለው። |
አቢሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ አለው፦ “ይህ ያደረግህብን ምንድነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት ያመጣህብን ምን ብንበድልህ ነው? ፈጽሞ የማይገባ ነገር በእኔ ፈጸምክብኝ።”
አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባርያውን ቃል ያድምጥ፤ ጌታ በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደሆነ፥ መሥዋዕት ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፥ በጌታ ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በጌታ ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳደውኛልና።