መሎጊያዎቹ ረጃጅሞች ስለ ሆኑ ጫፎቻቸው በቤተ መቅደሱ ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ይታይ ነበር፤ በውጭ በኩል ግን አይታዩም፤ እስከ ዛሬ ድረስም በዚያው ይገኛሉ።
ዘፀአት 25:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ሥራ፥ በወርቅም ለብጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ በወርቅም ለብጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለታቦቱ መሸከሚያ የሚሆኑ መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሥራ፤ በወርቅም ለብጣቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሎጊያዎችንም ከማይነቅዝ ዕንጨት ሥራ፤ በወርቅም ለብጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሥራ፥ በወርቅም ለብጣቸው። |
መሎጊያዎቹ ረጃጅሞች ስለ ሆኑ ጫፎቻቸው በቤተ መቅደሱ ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ይታይ ነበር፤ በውጭ በኩል ግን አይታዩም፤ እስከ ዛሬ ድረስም በዚያው ይገኛሉ።
አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፥ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ።
በእርሱም ላይ የሚገለገሉባቸውን የመሠውያውን ዕቃዎች ሁሉ፥ ጀሞዎቹን ሜንጦቹንም መጫሪያዎቹንም ጐድጓዳ ሳሕኖቹንም፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም ላይ የአቆስጣን ቁርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።
በእርሱም ላይ የአስቆጣውን ቁርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፥ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።