ዘፀአት 23:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊትህም ተርብ እሰድዳለሁ፥ ኤዊያዊውንም ከነዓናዊውንም ኬጢያዊውንም ከፊትህ አባርራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤዊያውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጢያውያንን ከመንገድህ ለማስወጣት ተርብን በፊትህ እሰድዳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጠላቶችህ ላይ ሽብር እልክባቸዋለሁ። አንተም ወደ ፊት ስትሄድ ሒዋውያንን፥ ከነዓናውያንንና ሒታውያንን ከፊትህ አባርራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊትህም ተርብ እሰድዳለሁ፤ አሞራዊውንም፥ ኤዌዎያዊውንም፥ ከነዓናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም ከፊትህ ያባርራቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊትህም ተርብ እሰድዳለሁ፥ ኤዊያዊውንም ከነዓናዊውንም ኬጢያዊውንም ከፊትህ አባርራለሁ። |