አንተ ከውጭ ሆነህ ጠብቅ፤ ያበደርኸውም ሰው መያዣውን ከቤት ያምጣልህ።
አንተ ውጪ ቈይ፤ እርሱ ራሱ መያዣውን ያምጣልህ።
አንተ ግን በውጭ ቁም፤ ያበደርኸውም ሰው መያዣውን ወደ ውጭ ያውጣልህ።
አንተ በውጭ ቁም ያበደርኸውም ሰው መያዣውን ያውጣልህ።
ራቁታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፥ በብርድ ጊዜ የሚደረብ የላቸውም።
“ማናቸውንም ነገር ለባልንጀራህ ስታበድር መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ለመቀበል ወደ ቤቱ አትግባ።
ሰውየው ድኻ ከሆነ፥ መያዣውን ከአንተ ዘንድ አታሳድርበት።