La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 20:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለመብል የማይሆኑትን የምታውቃቸውን ዛፎች ታጠፋቸዋለህ፥ ትቆርጣቸዋለህ፥ እስክታሸንፋትም ድረስ በምትዋጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመሽጋለህ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሚበላ ፍሬ እንደማያፈራ የምታውቀውን ዛፍ ግን ልትቈርጠውና ጦርነት የምታካሂድባትን ከተማ በድል እስክትቈጣጠራት ድረስ ለከበባው ምሽግ መሥሪያ ልትጠቀምበት ትችላለህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፍሬ የማያፈሩትን ሌሎች ዛፎች ግን እየቈረጥህ በመከመር ከተማይቱ እስከምትማረክበት ጊዜ ድረስ ለከበባ ተግባር ልትጠቀምባቸው ትችላለህ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለመ​ብል የማ​ይ​ሆ​ኑ​ትን የም​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን ዛፎች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ትቈ​ር​ጣ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ እስ​ክ​ታ​ሸ​ን​ፋ​ትም ድረስ በም​ት​ዋ​ጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመ​ሽ​ጋ​ለህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለመብል የማይሆኑትን የምታውቃቸውን ዛፎች ታጠፋቸዋለህ፥ ትቈርጣቸውማለህ፤ እስክታሸንፋትም ድረስ በምትዋጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመሽጋለህ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 20:20
10 Referencias Cruzadas  

የተመሸጉና ምርጥ የሆኑ ከተሞቻቸውን ሁሉ ድል አድርጋችሁ ትይዛላችሁ፤ የፍራፍሬ ዛፎቻቸውን ሁሉ ትቆርጣላችሁ፤ ምንጮቻቸውን ትደፍናላችሁ፤ ለም የሆኑ የእርሻ ቦታዎቻቸውን በማበላሸት ድንጋይ ትከምሩባቸዋላችሁ።”


በኢየሩሳሌምም በብልሃተኞች እጅ የተሠሩትን፥ በግንብና በቅጥር ላይ የሚቀመጡትን፥ ፍላጻና መርግ የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች ሠራ፤ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በድንቅ ረድቶታልና ዝናው እስከ ሩቅ አገር ድረስ ተሰማ።


ታናሽ ከተማ ነበረች፥ ጥቂቶች ሰዎችም ነበሩባት፥ ታላቅ ንጉሥም መጣባት ከበባትም፥ ታላቅ ግንብም ሠራባት።


“ስለዚህም ጌታ ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ወደዚች ከተማ አይመጣም፥ ፍላጻንም አይወረውርባትም፥ በጋሻም አይመጣባትም፥ የአፈርንም አይደለድልባትም።


ከሰይፍ ፊትና ከከበባት የአፈር ድልድል ለመከላከል ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላልና፦


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “ዛፎችዋን ቁረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ አፈርን ደልድሉ፤ ይህች ከተማ የምትቀሠፍ ናት፤ በመካከልዋ ያለው ነገር ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።


ብዙ ነፍሳትን ለማስወገድ ጉብታ በደለደሉ፥ ቅጥርንም በሠሩ ጊዜ፥ ፈርዖን ከኃያል ሠራዊቱና ከታላቅ ጉባኤው ጋር በጦርነት አይረዳውም።


ወዴትስ እንወጣለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል፥ ከተሞቹም ታላላቆች የተመሸጉም እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው፥’ ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አወኩት።


“አንድን ከተማ ተዋግተህ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ ካደረግህ፥ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፈህ አታጥፋ፤ የእነርሱን ፍሬ መብላት ትችላለህና አትቁረጣቸው፤ ከበህ የምታጠፋቸው የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን?


“አምላክህ ጌታ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር አንድ ሰው ተገድሎ ሜዳ ላይ ቢገኝና ገዳዩም ማን እንደሆነ ባይታወቅ፥