ዘዳግም 19:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ለአንተ በሚተላለፍልህ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልጀራህን የድንበር ምልክት አታንሣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ለአንተ በሚተላለፍልህ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አታንሣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ለአንተ በተሰጠው ድርሻና በጐረቤትህ መካከል በቀድሞ ትውልድ የተተከለውን የድንበር ምልክት አታፍርስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር፤ በምትካፈላት ርስትህ አባቶችህ የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር በምትወርሳት ርስትህ የቀደሙ ሰዎች የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል። |
በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ “ጌታ አምላካችሁ ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ የእናንተ ጦር ሰዎች ሁሉ ታጥቀው በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።