ዘዳግም 1:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግ፥ ትሄዱበት ዘንድ የሚገባውንም መንገድ ለማሳየት ሌሊት በእሳት፥ ቀን በደመና በፊታችሁ በመንገድ ሲሄድ የነበረውን ጌታ አምላካችሁን አላመናችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጕዞ ላይ ሳላችሁ የምትሰፍሩባቸውን ቦታዎች ለመፈለግና የምትሄዱበትን መንገድ ለማሳየት እርሱ ሌሊት በእሳት፣ ቀን በደመና ይመራችሁ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ስፍራን እንዲመርጥላችሁ፥ ትሄዱበትም ዘንድ የሚገባውን መንገድ እንዲያሳያችሁ ሌሊት በእሳት፥ ቀን በደመና በፊታችሁ በመንገድ ሲሄድ የነበረውን አላመናችሁትም። |
ከጌታም ተራራ ተነሥተው የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የጌታም የኪዳኑ ታቦት የሚያርፉበትን ስፍራ ለመፈለግ የሦስት ቀን መንገድ ቀድሞአቸው ተጓዘ።
ለዚችም ምድር ሰዎች ይናገራሉ። አቤቱ፥ አንተ በዚህ ሕዝብ መካከል እንደሆንህ ሰምተዋል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ ፊት ለፊት ተገልጠሃል፥ ደመናህም በላያቸው ቆሞአል፥ በቀንም በደመና ዓምድ፥ በሌሊትም በእሳት ዓምድ በፊታቸው ትሄዳለህ።