Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 14:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ንጋትም በሆነ ጊዜ ጌታ በእሳትና በደመና ዓምድ ሆኖ የግብፃውያንን ሠፈር ተመለከተ፥ የግብፃውያንንም ሠፈር አወከ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ሲነጋጋም እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዐምድ ሆኖ የግብጻውያንን ሰራዊት ቍልቍል ተመለከተ፤ በግብጻውያን ሰራዊት ላይም ሽብር ላከባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ገና ጎሕ ሳይቀድ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዐምድ ሆኖ የግብጻውያንን ሠራዊት በተመለከተ ጊዜ ሁሉም በፍርሃት ተጨነቁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ንጋ​ትም በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳ​ትና በደ​መና ዐምድ ሆኖ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ሠራ​ዊት ተመ​ለ​ከተ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት አወከ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ንጋትም በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዓምድ ሆኖ የግብፃውያንን ሠራዊት ተመለከተ፤ የግብፃውያንንም ሠራዊት አወከ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 14:24
16 Referencias Cruzadas  

አንተም፦ “እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን?


እነርሱ በእኩለ ሌሊት በድንገት ይሞታሉ፥ ሕዝቡ ተንቀጥቅጦ ያልፋል፥ ኃያላንም ያለ ምንም ድካም ይወገዳሉ።


ሕዝብንም ሆነ ሰውን በተመለከተ፥ ዝም ቢል የሚፈርድ ማን ነው? ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?


ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልከት፥ ዝቅ ዝቅም አድርገው፥ በደለኞችንም ወዲያውኑ እርገጣቸው።


ምድርን ያያል እንድትንቀጠቀጥም ያደርጋል፥ ተራሮችን ይዳስሳል፥ ይጤሳሉም።


እነሆ፥ ነገሥታት ተከማችተው በአንድነት መጥተዋል።


ቀን በደመና መራቸው፥ ሌሊቱንም ሁሉ በእሳት ብርሃን።


ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓት ነውና።


በቀንና በሌሊትም እንዲጓዙ፥ ጌታ ቀን በደመና ዓምድ መንገድ ሊመራቸው፥ ሌሊት ደግሞ በእሳት ዓምድ ሊያበራላቸው ከፊታቸው ይሄድ ነበር።


የሰረገሎቹንም ጎማ አሰረ፥ ወደ ጭንቅም አስገባቸው፤ ግብፃውያንም፦ “ጌታ ግብፃውያንን ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።


በጠላቶቻቸውም ፊት ተማርከው ቢሄዱ እንኳ ከዚያ ሰይፍን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይገድላቸዋል፤ ዓይኔንም በእነርሱ ላይ ለክፋት እንጂ ለመልካም አላደርግም።”


በማግስቱ ሳኦል ሠራዊቱን ከሦስት ቦታ ከፈለው፤ ሊነጋጋ ሲል የአሞናውያንን ሰፈር ጥሰው በመግባት ፀሓይ ሞቅ እስኪል ድረስ ፈጇቸው። በሕይወት የተረፉትም ሁለት እንኳን ሆነው በአንድ ላይ ሊሆኑ እስከማይችሉ ድረስ ተበታተኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos