La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 7:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በግብጽ ያሉትን የሕዝቤን መከራ ፈጽሜ አይቼ መቃተታቸውንም ሰምቼ ላድናቸው ወረድሁ፤ አሁንም ና፤ ወደ ግብጽ እልክሃለሁ፤’ አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በርግጥ አይቻለሁ፤ የጭንቅ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ላድናቸውም ወርጃለሁ። አሁንም ና፤ ወደ ግብጽ መልሼ እልክሃለሁ።’

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጽኑ መከራ በእርግጥ አይቼአለሁ፤ የጭንቀት ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ላድናቸው ወርጃለሁ፤ አሁንም ና! እኔ አንተን ወደ ግብጽ እልክሃለሁ።’

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በግ​ብፅ ያሉ​ትን የወ​ገ​ኖ​ችን መከራ ማየ​ትን አይ​ቻ​ለሁ፤ ጩኸ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰም​ቻ​ለሁ፤ ላድ​ና​ቸ​ውም ወር​ጃ​ለሁ፤ አሁ​ንም ና ወደ ግብፅ ሀገር ልላ​ክህ።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በግብፅ ያሉትን የሕዝቤን መከራ ፈጽሜ አይቼ መቃተታቸውንም ሰምቼ ላድናቸው ወረድሁ፤ አሁንም ና፥ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ’ አለው።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 7:34
21 Referencias Cruzadas  

ጌታም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።


ስለዚህ ኑ! እንውረድ፥ እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።”


እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸትዋ አድርገው እንደሆነ ወርጄ አያለሁ፥ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ።”


“በግብጽ የአባቶቻችንን መከራ አየህ፥ በቀይ ባሕርም ጩኸታቸውን ሰማህ፤


አገልጋዩን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ።


እርሱ ግን ጩኸታቸውን በሰማ ጊዜ ጭንቃቸውን ተመለከተ፥


አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው ውረድም፥ ተራሮችን ዳስሳቸው ይጢሱም።


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ “የምኖር እኔ ነኝ” አለው፤ ስለዚህ ለእስራኤል ልጆች፦ “‘የምኖር’ ወደ እናንተ ላከኝ በላቸው” አለው።


ሕዝቡም አመኑ፤ ጌታ የእስራኤልን ልጆች እንደተመለከተ ጭንቀታቸውንም እንዳየ በሰሙ ጊዜ፥ አጎነበሱ ሰገዱም።


ምነው ሰማያትን ቀደህ ብትወርድ! ምነው ተራሮችም ቢናወጡ!


ያዕቆብ ወደ አራም ምድር ሸሸ፥ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፥ ስለ ሚስትም በጎችን ያሰማራ ነበረ።


ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁና፤ በፊትህም ሙሴን፥ አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።


እኔም እወርዳለሁ፥ በዚያም ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፥ በአንተ ካለውም መንፈስ ወስጄ በእነርሱ ላይ አኖረዋለሁ፤ አንተም ብቻህን እንዳትሸከም የሕዝቡን ሸክም ከአንተ ጋር ይሸከማሉ።


ከሰማይም ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፤ እርሱም የሰው ልጅ ነው።


ፈቃዴን ለማድረግ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።


ጌታ መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ ከመስፍኑ ጋር ስለሚሆን፥ እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ጌታ ከጠላቶቻቸው ያድናቸው ነበር፤ ከጠላቶቻቸው ሥቃይና መከራ ሲደርስባቸው በሚጮኹበት ጊዜ ጌታ ይራራላቸው ነበር።