ሐዋርያት ሥራ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፍርግያም በጵንፍልያም በግብጽም በቀሬናም በኩል ባሉት በሊቢያ ወረዳዎች የምንኖር፥ በሮሜም የምንቀመጥ፥ አይሁድም ወደ ይሁዲነትም የገባን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፍርግያ፣ በጵንፍልያ፣ በግብጽ፣ በቀሬና አጠገብ ባሉት በሊቢያ አውራጃዎች የምንኖር፣ ከሮም የመጣን አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፍርግያ፥ በጵንፍልያ፥ በግብጽ፥ በቀሬና አጠገብ ባሉት በሊቢያ አውራጃዎች የምንኖር ነን፤ ከሮምም የመጣን አይሁድና ወደ አይሁድነትም የገባን እንገኛለን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍርግያ፥ በጵንፍልያ፥ በግብፅ፥ በሊብያ አውራጃ፥ በቀርኔን የምንኖር፥ ከሮሜም የመጣን አይሁድ፥ መጻተኞችም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፍርግያም በጵንፍልያም በግብፅም በቀሬናም በኩል ባሉት በሊቢያ ወረዳዎች የምንኖር፥ በሮሜም የምንቀመጥ፥ አይሁድም ወደ ይሁዲነትም የገባን፥ |
እንዲሁም የእስራኤል ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነውና፥ አሕዛብም ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና ግብጽንና ይሁዳን፥ ኤዶምያስንም፥ የአሞንንም ልጆች፥ ሞአብንም፥ በምድረ በዳም የተቀመጡትን ጠጉራቸውን በዙሪያ የተላጩትን ሁሉ በዚያን ዘመን እቀጣለሁ።”
የሠራዊት ጌታም እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከሁሉም የአሕዛብ ቋንቋ ዐሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና እኛም ከእናንተ ጋር እንሂድ” ይላሉ።
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ፥ አንድ ሰው የእምነታችሁ ተከታይ ለማድረግ በባሕርና በደረቅ ትዞራላችሁ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ታደርጉታላችሁ።
ከእነርሱ ግን የቆጵሮስና የቀሬና ሰዎች የነበሩት አንዳንዶቹ ወደ አንጾኪያ መጥተው የጌታን የኢየሱስን ወንጌል እየሰበኩ ለግሪክ ሰዎች ተናገሩ።
በአንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርሲቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ።
ጉባኤውም ከተፈታ በኋላ ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ገብተው ከሚያመልኩ ብዙዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሉአቸው፤ እነርሱም ሲነግሩአቸው በእግዚአብሔር ጸጋ ጸንተው እንዲኖሩ አስረዱአቸው።
ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፤ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፤ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና።
በወገኑም የጳንጦስ ሰው የሚሆን አቂላ የሚሉትን አንድ አይሁዳዊ አገኘ፤ እርሱም ከጥቂት ጊዜ በፊት ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር ከኢጣልያ መጥቶ ነበር፤ አይሁድ ከሮሜ ይወጡ ዘንድ ቀላውዴዎስ አዞ ነበርና፤ ወደ እነርሱ ቀረበ፤
በሁለተኛውም ሌሊት ጌታ በአጠገቡ ቆሞ “ጳውሎስ ሆይ! በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርህ እንዲሁ በሮሜም ትመሰክርልኝ ዘንድ ይገባሃልና አይዞህ፤” አለው።
ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ሰምተው እስከ አፍዩስ ፋሩስና ሦስት ማደሪያ እስከሚባለው ሊቀበሉን ወጡ፤ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ልቡም ተጽናና።
ይህም ቃል ሕዝቡን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤ እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም ጢሞናንም ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።
የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና በእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤
በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁ፥ በሮሜ ላላችሁ ሁሉ፥ ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።