2 ቆሮንቶስ 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርግጥ ያ ከብሮ የነበረው እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት ክብሩን አጥቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በፊት ክቡር የነበረው የላቀ ክብር ካለው ጋራ ሲወዳደር ክብር የሌለው ሆኗል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኋለኛው ክብር እጅግ የላቀ ከመሆኑ የተነሣ ያለፈው ክብር ምንም እንዳልነበረው ይቈጠራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ፍጹም ክብር ባነጻጸሯት ጊዜ የከበረችው እንዳልከበረች ትሆናለችና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚህ ነገር ክብሩን አጥቶአልና። |
ከግርማዊው ክብር “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው!” የሚል ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ገናናነትን ተቀብሏል።
ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።