ገንዳውም ከነሐስ በተሠሩ ዐሥራ ሁለት የበሬዎች ምስሎች ጀርባ ላይ ተቀመጠ፤ ኰርማዎቹም በየአቅጣጫው ፊታቸውን ወደ ውጪ መልሰው ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ሦስቱ ወደ ምዕራብ የሚመለከቱ ይመስሉ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 4:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓሥራ ሁለትም በሬዎችም ምስል ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ከእነርሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን ሦስቱም ወደ ምዕራብ ሦስቱም ወደ ደቡብ ሦስቱም ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር፤ ኩሬውም በእነርሱ ላይ ተቀምጦ ነበረ፥ የሁሉም ጀርባቸው በስተ ውስጥ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገንዳውም፣ ሦስቱ ፊታቸውን ወደ ሰሜን፣ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ባዞሩ የዐሥራ ሁለት በሬዎች ምስሎች ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ገንዳው በላያቸው ሆኖ የሁሉም የኋላ አካል በመካከል ላይ የገጠመ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በርሜሉም ከነሐስ በተሠሩና ፊታቸውን ወደ ውጪ ባዞሩ በዐሥራ ሁለት የበሬዎች ምስሎች ጀርባ ላይ ተቀምጦ ነበር፤ የኰርማዎቹ ምስሎችም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ፥ ሦስቱ ደግሞ ወደ ምዕራብ የሚመለከቱ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥራ ሁለት በሬዎችን ሠሩላቸው። ከእነርሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፥ ሦስቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስቱም ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር፤ ቀልጣ የተሠራች ኵሬም በላያቸው ነበረች፤ የሁሉም ጀርባቸው በስተውስጥ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዐሥራ ሁለትም በሬዎችም ምስል ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ከእነርሱም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱም ወደ ምዕራብ፥ ሦስቱም ወደ ደቡብ፥ ሦስቱም ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር፤ ኵሬውም በላያቸው ነበረ፤ የሁሉም ጀርባቸው በስተ ውስጥ ነበረ። |
ገንዳውም ከነሐስ በተሠሩ ዐሥራ ሁለት የበሬዎች ምስሎች ጀርባ ላይ ተቀመጠ፤ ኰርማዎቹም በየአቅጣጫው ፊታቸውን ወደ ውጪ መልሰው ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ሦስቱ ወደ ምዕራብ የሚመለከቱ ይመስሉ ነበር።
በበታቹም ለአንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአንድም ክንድ ዐሥር፥ እንደ በሬዎች ያሉ ቅርጾች በኩረው ላይ አዞረበት፤ ኩሬውንም በቀለጠ ጊዜ የበሬዎቹም ቅርጾች በሁለት ተራ ከእርሱ ጋር አብረው ቀልጠው ነበር።
ውፍረቱም አንድ ጋት ያህል ነበረ፤ ከንፈሩም እንደ ጽዋ ከንፈር፥ እንደ ሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ሦስት ሺህም የባዶስ መሥፈሪያ ይይዝ ነበር።