2 ዜና መዋዕል 2:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሁንም ኪራም-አቢ የሚባል ብልሃተኛና አስተዋይ ሰው ልኬልሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እጅግ ብልኀተኛ የሆነውን ኪራም አቢን ልኬልሃለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ ጥበበኛና በእጅ ሥራ የሠለጠነ ሑራም አቢ ተብሎ የሚጠራ ብልኀተኛ ሰው ልኬልሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ብልሃተኛና አስተዋይ ሰው አቢኪራምን ልኬልሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ከብልሃተኛዎችህ ጋር ከጌታዬም ከአባትህ ከዳዊት ብልሃተኞች ጋር ይሆን ዘንድ ኪራምአቢ የሚባል ብልሃተኛና አስተዋይ ሰው ሰድጄልሃለሁ። |
እንዲሁም ኪራም እንዲህ አለ፦ “ሰማይንና ምድርን የፈጠረ፥ ለጌታም ቤተ መቅደስ ለመንግሥቱም ቤተ መንግሥት እንዲሠራ ጥበበኛና ብልሃተኛ አስተዋይም ልጅ ለንጉሡ ለዳዊት የሰጠ የእስራኤል አምላክ ጌታ ቡሩክ ይሁን።
እናቱ ከዳን ልጆች ናት፥ አባቱም የጢሮስ ሰው ነው፤ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንና ብረቱን፥ ድንጋይንና እንጨቱን፥ ሐምራዊውንና ሰማያዊውን ቀዩንም ግምጃ፥ ጥሩውንም በፍታ ለመሥራት፥ ቅርጽም ለመሥራት ንድፍም ለመንደፍ ሌላም ነገር ሁሉ ለማድረግ እውቀት አለው፥ እርሱም ከብልሃተኛዎችህ ጋር ከጌታዬም ከአባትህ ከዳዊት ብልሃተኞች ጋር አብሮ ይሁን።
አሁንም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው በእኔ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት ብልሃተኞች ጋር አብሮ የሚሆን፥ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንና ብረቱን፥ ሐምራዊውንና ቀዩን ሰማያዊውንም ግምጃ የሚሠራ፥ ቅርጽንም የሚያውቅ ብልሃተኛ ሰው ላክልኝ።