Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አሁ​ንም ብል​ሃ​ተ​ኛና አስ​ተ​ዋይ ሰው አቢ​ኪ​ራ​ምን ልኬ​ል​ሃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “እጅግ ብልኀተኛ የሆነውን ኪራም አቢን ልኬልሃለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “አሁንም ኪራም-አቢ የሚባል ብልሃተኛና አስተዋይ ሰው ልኬልሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “እነሆ ጥበበኛና በእጅ ሥራ የሠለጠነ ሑራም አቢ ተብሎ የሚጠራ ብልኀተኛ ሰው ልኬልሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አሁንም ከብልሃተኛዎችህ ጋር ከጌታዬም ከአባትህ ከዳዊት ብልሃተኞች ጋር ይሆን ዘንድ ኪራምአቢ የሚባል ብልሃተኛና አስተዋይ ሰው ሰድጄልሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 2:13
5 Referencias Cruzadas  

የእ​ግር መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን፥ የእጅ መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን፥ ጋኖ​ችን፥ የሥጋ ማውጫ ሜን​ጦ​ዎ​ች​ንና ኪራም የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ከን​ጹሕ ናስ ሠርቶ ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አቀ​ረ​በ​ለት።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ልኮ ኪራ​ምን ከጢ​ሮስ አስ​መጣ።


አሁ​ንም በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስና በብ​ረት፥ በሐ​ም​ራ​ዊና በቀይ፥ በሰ​ማ​ያ​ዊም ግምጃ መለ​በጥ የሚ​ች​ልና፥ አባቴ ዳዊት ካዘ​ጋ​ጃ​ቸው በእኔ ዘንድ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ካሉት ብል​ሃ​ተ​ኞች ጋር ቅርጽ ማው​ጣት የሚ​ያ​ውቅ ብል​ሃ​ተኛ ሰውን ላክ​ልኝ።


የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራ​ምም ደግሞ አለ፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ለመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ቤት ይሠራ ዘንድ ጥበ​በ​ኛና ብል​ሃ​ተኛ፥ አስ​ተ​ዋ​ይም ልጅ ለን​ጉሡ ለዳ​ዊት የሰጠ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን የፈ​ጠረ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ይሁን።


እናቱ ከዳን ልጆች ናት፤ አባ​ቱም የጢ​ሮስ ሰው ነው፤ በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስና በብ​ረት፥ ድን​ጋ​ዩ​ንና እን​ጨ​ቱን መለ​በጥ፥ ሐም​ራ​ዊ​ው​ንና ሰማ​ያ​ዊ​ውን፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ጥሩ​ው​ንም በፍታ መሥ​ራት፥ ቅር​ጽም፥ ሌላም ነገር ሁሉ ማድ​ረግ ያው​ቃል። ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችህ ጋር ከጌ​ታ​ዬም ከአ​ባ​ትህ ከዳ​ዊት ብል​ሃ​ተ​ኞች ጋር ሥራ ብለህ የም​ት​ሰ​ጠ​ውን ሁሉ አስቦ መሥ​ራት ይች​ላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios