2 ዜና መዋዕል 14:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳም ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው፤ ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ፥ በጌታና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና፤ የይሁዳ ሰዎችም እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሳና ሰራዊቱም እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዷቸው፤ እጅግ ብዙ ቍጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ስለ ወደቁም፣ ሊያንሰራሩ አልቻሉም፤ በእግዚአብሔር ፊትና በሰራዊቱ ፊት ተደመሰሱ። የይሁዳም ሰዎች እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሳና ሠራዊቱም እስከ ገራር ድረስ አሳደዱአቸው፤ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ብዙ ሰዎች ስላለቁ፥ ሠራዊቱ እንደገና ተንሠራርቶ ሊዋጋ አልቻለም፤ በዚህም ዐይነት ኢትዮጵያውያን በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ድል ሆኑ፤ የይሁዳ ሰዎችም እጅግ የበዛ ምርኮ ወሰዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሳም፥ ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌዶር ሀገር ድረስ አሳደዱአቸው፤ ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ፤ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና፤ እጅግም ብዙ ምርኮ ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳም ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው፤ ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ፤ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና፤ እጅግም ብዙ ምርኮ ወሰዱ። |
በዚህ ዓይነት የከነዓናውያን ድንበር ከሲዶና አንሥቶ፥ በገራር አጠገብ እስካለው እስከ ጋዛ ድረስ፥ ወደ ሰዶም እና ገሞራ፥ አዳማና በላሻዕ አጠገብ እስካለው እስከ ጸቦይም ድረስ ይደርሳል።
እርሱም ሺህ ሁለት መቶ ሰረገሎችና ስልሳ ሺህ ፈረሰኞች ይዞ ነበር። ከእርሱም ጋር ከግብጽ ለመጣው ሕዝብ ቍጥር አልነበረውም፤ እነርሱም የልብያ ሰዎች ሱካውያን፥ የኢትዮጵያ ሰዎችም ነበሩ።
ከጌታም ዘንድ ታላቅ ድንጋጤ ስለ ያዛቸው በጌራራ ዙሪያ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ ድል በማድረግ በከተሞቹም ውስጥ እጅግ ብዝበዛ ነበርና ከተሞቹን ሁሉ በዘበዙ።
እርሱም፦ “አይደለሁም፤ እኔ የጌታ ሠራዊት አዣዥ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ” አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ “ጌታዬ ለባርያው የሚነግረው ምንድነው?” አለው።
ጌታዬ የጌታን ጦርነት ስለሚዋጋ ጌታም ለጌታዬ የታመነ ቤት በእርግጥ ለዘለዓለም የሚያጸናለት በመሆኑ፥ እባክህ የእኔን የአገልጋይህን በደል ይቅር በል፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህ።