ከዚያም ዳዊት አቢሳንና አገልጋዮቹን ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “ከአብራኬ የወጣ ልጅ ሕይወቴን ሊያጠፋት ከፈለገ፥ ይህ ብንያማዊ ቢያደርገው ምን ያስደንቃል? ስለዚህ ተዉት፤ ጌታ በል ብሎት ነውና ይራገም፤
1 ጢሞቴዎስ 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም በመረዳት ሕግ የተሠራው ለጻድቃን ሳይሆን ይልቁንስ ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዐመጸኞችና ለኀጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኩሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥ ለነፍሰ ገዳዮች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ሕግ የተሰጠው ለጻድቃን ሳይሆን፣ ለሕግ ተላላፊዎችና ለዐመፀኞች፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር ለሌላቸውና ለኀጢአተኞች፣ ቅድስና ለሌላቸውና እግዚአብሔርን ለሚንቁ፣ አባትና እናታቸውን ለሚገድሉ፣ ለነፍሰ ገዳዮች መሆኑን እናውቃለን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ሕግ የተሠራው ለደጋግ ሰዎች እንዳልሆነ እናውቃለን፤ ሕግ የተሠራው ለዐመፀኞችና ለወንጀለኞች፥ እግዚአብሔርን ለማያመልኩና ለኃጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና መንፈሳዊ ነገርን ለሚንቁ፥ አባትንና እናትን ለሚገድሉና ለነፍሰ ገዳዮች፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዐመጸኞችና ለኀጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኵሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥ ለነፍሰ ገዳዮችና ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለውሸተኞችም በውሸትም ለሚምሉ፥ የብሩክ እግዚአብሔርንም ክብር እንደሚገልጥ ለእኔ አደራ እንደ ተሰጠኝ፥ ወንጌል የሆነውን ደኅና ትምህርት ለሚቃወም ለሌላ ነገር ሁሉ ሕግ እንደ ተሠራ እንጂ ለጻድቅ እንዳልተሠራ በማወቅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይኸውም፥ ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዓመጸኞችና ለኃጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኵሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥ ለነፍሰ ገዳዮችና ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለውሸተኞችም በውሸትም ለሚምሉ፥ የብሩክ እግዚአብሔርንም ክብር እንደሚገልጥ ለእኔ አደራ እንደ ተሰጠኝ ወንጌል የሆነውን ደኅና ትምህርት ለሚቃወም ለሌላ ነገር ሁሉ ሕግ እንደ ተሰራ እንጂ ለጻድቅ እንዳልተሰራ ሲያውቅ ነው። |
ከዚያም ዳዊት አቢሳንና አገልጋዮቹን ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “ከአብራኬ የወጣ ልጅ ሕይወቴን ሊያጠፋት ከፈለገ፥ ይህ ብንያማዊ ቢያደርገው ምን ያስደንቃል? ስለዚህ ተዉት፤ ጌታ በል ብሎት ነውና ይራገም፤
ከዕለታት በአንዱ ቀን ኒስሮክ በሚል ስም በሚጠራው ባዕድ አምላኩ ቤተ መቅደስ ውስጥ በስግደት ላይ እንዳለ፥ ከልጆቹ ሁለቱ በተለይ አድራሜሌክና ሣሬጼር ተብለው የሚጠሩት በሰይፍ ገደሉት፤ እነርሱም ወደ አራራት አምልጠው ሄዱ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ከልጆቹ አንዱ አስራዶ የተባለው ነገሠ።
ጌታም ጽኑዓን ኃያላኑንና መሳፍንቱን የጦር አዛዦቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር እንዲያጠፋ መልአኩን ላከ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከአብራኩ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።
ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ መሶልሶል፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜ እንደ ነገርኋችሁ፥ አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
ነገር ግን ከረከሰው ከዚህ ዓለም አፈ ታሪክና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አለማምድ።
ሰዎች እንዲህ ይሆናሉና፤ ራሳቸውን የሚወዱ፥ ገንዘብን ወዳጆች፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባርያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት ጊዜያችንን የምናሳልፍ፥ የምንጠላ፥ እርስ በርሳችንም የምንጠላላ ነበርን።
እነዚህ ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በውሃ የዳኑት ጥቂት ሲሆኑ እነርሱም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ።
ይህም በሁሉ ላይ ለመፍረድ ነው፤ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኀጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዐመፀኞችም ኀጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኀጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ”
ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”