1 ሳሙኤል 14:48 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጀግንነት ተዋግቶ አማሌቃውያንን አሸነፈ፤ እስራኤልንም ይዘርፏቸው ከነበሩት እጅ ታደጋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጀግንነት ተዋግቶ አማሌቃውያንን አሸነፈ፤ እስራኤልንም ይዘርፏቸው ከነበሩት እጅ ታደጋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጀግንነትም ተዋግቶ የዐማሌቅን ሕዝብ እንኳ ሳይቀር ድል መታ፤ እርሱም እስራኤላውያንን ከጠላቶቻቸው እጅ አዳነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ጀግና ነበረ፤ አማሌቃውያንንም መታ፤ እስራኤልንም ከዘራፊዎቹ እጅ አዳነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ጀግና ነበረ፥ አማሌቃውያንንም መታ፥ እስራኤልንም ከዘራፊዎቹ እጅ አዳነ። |
ጌታም ሙሴን፦ “ይህንን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ አኑረው፥ የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና” አለው።
ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፥ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ መደምሰስን፥ ይህንን አትርሳ።”