እያንዳንዱም ውጊያ የገጠመውን ጠላቱን ገደለ፤ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤላውያንም ያሳድዱአቸው ጀመር፤ ቤንሀዳድ ግን በፈረሱ ላይ በመቀመጥ ከጥቂት ፈረሰኞች ጋር ሸሽቶ አመለጠ።
1 ነገሥት 20:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ አክዓብም ወደ ጦሩ ሜዳ ገብቶ የጠላትን ፈረሶችና ሠረገሎች ማረከ፤ በሶርያውያንም ላይ ታላቅ ጥፋት በማድረስ ድል አደረጋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብም ወደ ፊት በመግፋት ፈረሶችንና ሠረገሎችን ማረከ፤ በሶርያውያንም ላይ ከባድ ጕዳት አደረሰባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ አክዓብም ወደ ጦሩ ሜዳ ገብቶ የጠላትን ፈረሶችና ሠረገሎች ማረከ፤ በሶርያውያንም ላይ ታላቅ ጥፋት በማድረስ ድል አደረጋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ክፉ ነገር አመጣብሃለሁ፤ እሳትን ከኋላህ አነድዳለሁ፤ ዐጥር ተጠግቶ እስከሚሸን ድረስ የአክዓብን ዘር አጠፋዋለሁ፤ በእስራኤል ውስጥ ያሉትንም፥ የሌሉትንም እነቅላለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ክፉ ነገር አመጣብሃለሁ፤ ፈጽሞም እጠርግሃለሁ፤ ከአክዓብም በእስራኤል ዘንድ የታሰረውንና የተለቀቀውን ወንድ ሁሉ አጠፋለሁ፤ |
እያንዳንዱም ውጊያ የገጠመውን ጠላቱን ገደለ፤ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤላውያንም ያሳድዱአቸው ጀመር፤ ቤንሀዳድ ግን በፈረሱ ላይ በመቀመጥ ከጥቂት ፈረሰኞች ጋር ሸሽቶ አመለጠ።
ከዚህ በኋላ ነቢዩ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ የሶርያ ንጉሥ በሚመጣው የጸደይ ወራት እንደገና አደጋ ስለሚጥልብህ “ተመልሰህ ሂድና ሠራዊትህን በማጠናከር አደራጅ፤ ጥንቃቄ የሞላበትንም የጦርነት ስልት አዘጋጅ” አለው።
ነገር ግን እነርሱ ወደ ሰፈር በደረሱ ጊዜ እስራኤላውያን ተነሥተው አደጋ በመጣል ወደ ኋላ መለሱአቸው፤ እስራኤላውያን አገሪቱን ወረው ሞዓባውያንን ጨፈጨፉአቸው።
እስኪጠፉም ድረስ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች በጽኑ ውግያ ድል ማድረጋቸውን በፈጸሙ ጊዜ፥ ከእነርሱም ያመለጡት ወደ ተመሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥
ከአሮዔር አንሥቶ እስከ ሚኒት አካባቢ ከዚያም አልፎ እስከ ክራሚም የሚገኙትን ሃያ ከተሞች ፈጽሞ አጠፋቸው፤ አሞናውያንም ለእስራኤል ተገዙ።
እርሱም “ጠላታችሁን ሞዓብን ጌታ በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ተከተሉኝ” በማለት አዘዛቸው፤ እነርሱም ተከትለውት ወረዱ፤ ከዚያም ከዮርዳኖስ ወደ ሞዓብ የሚያሻግሩትን ስፍራዎች በመያዝ አንድም ሰው እንዳያልፍ ከለከሉ።
ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እየፎከሩ ፍልስጥኤማውያንን እስከ ጋት መግቢያና እስከ ዔቅሮን በሮች ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያንም ሬሳ ከሸዓራይም አንሥቶ እስከ ጋትና ከዚያም እስከ ዔቅሮን በሮች ባለው መንገድ ላይ ወደቀ።