Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 20:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዚህ በኋላ ነቢዩ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ የሶርያ ንጉሥ በሚመጣው የጸደይ ወራት እንደገና አደጋ ስለሚጥልብህ “ተመልሰህ ሂድና ሠራዊትህን በማጠናከር አደራጅ፤ ጥንቃቄ የሞላበትንም የጦርነት ስልት አዘጋጅ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚያም በኋላ ነቢዩ ወደ እስራኤል ንጉሥ መጥቶ፣ “በሚመጣው የጸደይ ወራት የሶርያ ንጉሥ ተመልሶ ይመጣብሃልና በርታ፤ ምን ማድረግ እንዳለብህም ዕወቅ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚህ በኋላ ነቢዩ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ የሶርያ ንጉሥ በሚመጣው የጸደይ ወራት እንደገና አደጋ ስለሚጥልብህ “ተመልሰህ ሂድና ሠራዊትህን በማጠናከር አደራጅ፤ ጥንቃቄ የሞላበትንም የጦርነት ስልት አዘጋጅ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በሥ​ራ​ህም አስ​ቈ​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አስ​ተ​ሃ​ልና ቤት​ህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ቤት እንደ አኪ​ያም ልጅ እንደ ባኦስ ቤት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በሥራህም አስቆጥተኸኛልና፥ እስራኤልንም አስተሃልና ቤትህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤት እንደ አኪያም ልጅ እንደ ባኦስ ቤት አደርገዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 20:22
20 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም በተከታዩ የጸደይ ወቅት ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ በእስራኤል ላይ አደጋ ለመጣል ወደ አፌቅ ከተማ ገሠገሠ።


ነገሥታት ለጦርነት በሚወጡበት በጸደይ ወራት ዳዊት ኢዮአብን ከአገልጋዮቹና ከመላው እስራኤል ጋር አዘመተው፤ እነርሱም አሞናውያንን አጠፉ፤ ራባ የተባለችውንም ከተማ ከበቡ፤ በዚህ ጊዜ ግን ዳዊት በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።


በዚህን ጊዜ አንድ ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “ጌታ ‘ከቤንሀዳድ ሠራዊት ብዛት የተነሣ አትፍራ! እኔ ዛሬ በዚህ ሠራዊት ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርጋለሁ፤ አንተም ደግሞ እኔ ጌታ መሆኔን ታውቃለህ’ ይልሃል” አለው።


እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መለወጫ ነገሥታት ወደ ጦርነት በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ ሠራዊቱን አወጣ፥ የአሞንንም ልጆች አገር አጠፋ፤ መጥቶም ረባትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ቈይቶ ነበር። ኢዮአብም ረባትን መትቶ አፈረሳት።


እኔ ጌታ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።


አቤቱ ጌታ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች።


እናንተ አሕዛብ፤ ፎክሩ፤ ግን ደንግጡ። በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤


አሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።


የጌታ ስም የጸና ግምብ ነው፥ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።


በጌታ ተስፋ አድርግ፥ በርታ፥ ልብህም ይጽና፥ በጌታ ተስፋ አድርግ።


አሜስያስም በረታ፥ ሕዝቡንም አውጥቶ ወደ ጨው ሸለቆ ሄደ፥ ከሴይርም ልጆች ዐሥር ሺህ ገደለ።


ብትሄድ ግን፥ በእነርሱም ማሸነፍን ብታስብ፥ የመርዳትና የመጣል ኃይል ከጌታ ዘንድ ነውና ጌታ በጠላቶችህ ፊት ይጥልሃል።”


ከእነርሱም አንዱ “ንጉሥ ሆይ፥ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው” ሲል መለሰለት።


አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።


ነቢዩ ማንነቱ እንዳይታወቅ ፊቱን በጨርቅ ሸፈነ፤ ሄዶም በዚያ በኩል የሚያልፈውን የእስራኤልን ንጉሥ ለመጠበቅ በመንገድ ዳር ቆመ።


ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።


በተረፈ በጌታ በኃይሉ ብርታትም ጠንክሩ።


ንጉሥ አክዓብም ወደ ጦሩ ሜዳ ገብቶ የጠላትን ፈረሶችና ሠረገሎች ማረከ፤ በሶርያውያንም ላይ ታላቅ ጥፋት በማድረስ ድል አደረጋቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios