ልንበላና ልንጠጣ መብት የለንምን?
ለመሆኑ፣ የመብላትና የመጠጣት መብት የለንምን?
እኛ ምግብና መጠጥ የማግኘት መብት የለንምን?
በውኑ ልንበላና ልንጠጣ አይገባንምን?
ፀሐይም በገባች ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ እንጀራው ነውና ከተቀደሰው ነገር ይበላል።
ለመንገዳችሁ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።
ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋልና እነርሱ የሚሰጡአችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያው ቤት ተቀመጡ። ከቤት ወደ ቤት አትዘዋወሩ።
ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤
ለሚመረምሩኝ መልሴ ይህ ነው።
ቃሉን የሚማር መልካሙን ነገር ሁሉ ከሚያስተምረው ጋር ይካፈል።
እንዲሁም ከእናንተም ሆነ ከሌሎች ክብርን አልፈለግንም፥
ወንድሞች ሆይ! ድካማችንንና ጥረታችንን ታስታውሱታላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እየሰበክን በአንዳችሁም ላይ እንኳ ሸክም ላለመሆን ስንል ሌሊትና ቀን እንሠራ ነበር።