1 ዜና መዋዕል 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብንያምም ልጆች የሐስኑአ ልጅ የሆዳይዋ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብንያማውያን፦ የሐስኑአ ልጅ፣ የሆዳይዋ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብንያም ነገድ በኢየሩሳሌም ለመኖር የሄዱት የሚከተሉት ናቸው፦ የሃሰኑአ ልጅ ሆዳውያ፥ የሆዳውያ ልጅ መሹላም፥ የመሹላም ልጅ ሳሉ፥ የይሮሐም ልጅ ዩብነያ፥ የሚክሪ የልጅ ልጅ የዑዚ ልጅ ኤላ፥ የዩብኒያ ልጅ ረዑኤል፥ የረዑኤል ልጅ ሸፋጥያ፥ የሸፋጥያ ልጅ መሹላም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብንያምም ልጆች የሐስኑአ ልጅ የሆዳይዋ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሎ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብንያምም ልጆች የሐስኑአ ልጅ የሆዳይዋ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ፤ |
የብንያምም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የይሻዕያ ልጅ፥ የኢቲኤል ልጅ፥ የማዓሤያ ልጅ፥ የቆላያ ልጅ፥ የፕዳያ ልጅ፥ የዮዔድ ልጅ የምሹላም ልጅ ሳሉ።
ጸሐፊውም ዕዝራ ለዚህ ተብሎ በተሠራ የእንጨት መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአጠገቡ ማቲትያ፥ ሼማዕ፥ ዓናያ፥ ኡሪያ፥ ሒልቅያና ማዓሴያ በቀኙ በኩል፤ ፐዳያ፥ ሚሻኤል፥ ማልኪያ፥ ሐሹም፥ ሐሽባዳና፥ ዘካርያስ፥ ሜሹላም በግራው በኩል ቆመው ነበር።