ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን፤ “ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ዐናቶት ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፤ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ትሸከም ስለ ነበርክ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም” አለው።
1 ዜና መዋዕል 6:60 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማሪያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብንያም ነገድ ድርሻ ላይ ገባዖንን፣ ጌባዕን፣ ጋሌማን፣ ዓናቶትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጡ። ለቀዓት ዘሮች የተከፋፈሉት እነዚህ ከተሞች በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በብንያም ግዛትም ጌባዕ፥ ዓሌሜትና ዐናቶት ተብለው የሚጠሩት ከተሞች ከነግጦሽ ቦታዎቻቸው ለአሮን ልጆች የተሰጡ ነበሩ፤ እንግዲህ ለአሮን ዘሮች ቤተሰብ ሁሉ መኖሪያ የሚሆኑ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓናቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማርያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማርያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ። |
ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን፤ “ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ዐናቶት ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፤ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ትሸከም ስለ ነበርክ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም” አለው።
ዮናታን ጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፥ “ዕብራውያን ይስሙት!” በማለት በሀገሩ ሁሉ መለከት አስነፋ።