1 ዜና መዋዕል 6:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግራቸውም በኩል ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቂሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥ የማሎክ ልጅ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስተ ግራቸው በኩል ዐብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጆች፤ የቂሳ ልጅ ኤታን፣ የአብዲ ልጅ፣ የማሎክ ልጅ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግራው በኩል የቆመው የሦስተኛው የመዘምራን ቡድን መሪ የመራሪ ልጅ ኤታን ነበር፤ የእርሱም የቤተሰብ የትውልድ ሐረግ ከዚህ በታች በተመለከተው አኳኋን እስከ ሌዊ ይደርሳል፦ ኤታን፥ ቂሺ፥ ዐብዲ፥ ማሉክ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግራቸውም በኩል የሚቆሙ ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቄሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥ የማሎክ ልጅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግራቸውም በኩል ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቂሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥ የማሎክ ልጅ፥ |
ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ ይሠሩ የነበሩት ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።
ከኤዶታም የኤዶታም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ጽሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መቲትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ክብር በመሰንቆ ትንቢት ከተናገረው ከአባታቸው ከኤዶታም ትእዛዝ በታች ነበሩ።
እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም እንዲዘምሩ፥ በእግዚአብሔርም ቤት እንዲያገለግሉ ከአባታቸው ትእዛዝ በታች ነበሩ፤ አሳፍም ኤዶታምም ኤማንም ከንጉሡ ትእዛዝ በታች ነበሩ።