የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 32:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የባ​ሕ​ሩን ውኃ እንደ ረዋት የሚ​ሰ​በ​ስ​በው፥ በቀ​ላ​ዮ​ችም መዝ​ገ​ቦች የሚ​ያ​ኖ​ረው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤ በድል ዝማሬም ትከብበኛለህ። ሴላ

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ከጭንቅ ትጠብቀኛለህ፥ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤ ስላዳንከኝ በከፍተኛ ድምፅ በደስታ እዘምራለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 32:7
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሳ​ኦል እጅና ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ እጅ ባዳ​ነው ቀን የዚ​ህን መዝ​ሙር ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ።


አቤቱ፥ በአ​ዲስ ምስ​ጋና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዐሥር አው​ታር ባለው በገ​ናም እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።


በፀ​ሐይ ውስጥ ድን​ኳ​ኑን አደ​ረገ፥ እር​ሱም እንደ ሙሽራ ከእ​ል​ፍኙ ይወ​ጣል፤ በመ​ን​ገዱ እን​ደ​ሚ​ራ​መድ አር​በኛ ደስ ይለ​ዋል።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ወደ እጆ​ቹም ተግ​ባር አላ​ሰ​ቡ​ምና አፍ​ር​ሳ​ቸው፥ አት​ሥ​ራ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሕ​ዛ​ብን ምክር ይመ​ል​ሳል፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ዐሳብ ይመ​ል​ሳል። የአ​ለ​ቆ​ችን ምክ​ራ​ቸ​ውን ያስ​ረ​ሳ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ዌው አልጋ ሳለ ይረ​ዳ​ዋል፤ መኝ​ታ​ው​ንም ሁሉ ከበ​ሽ​ታው የተ​ነሣ ይለ​ው​ጥ​ለ​ታል።


አንተ ጻድ​ቁን ትባ​ር​ከ​ዋ​ለ​ህና፤ አቤቱ፥ እንደ አላ​ባሽ ጋሻ ከለ​ል​ኸን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለድ​ሆች መጠ​ጊያ ሆና​ቸው፥ እር​ሱም በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ረዳ​ታ​ቸው ነው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን ይሻ​ላል፥ ልዑል ሆይ፥ ለስ​ም​ህም መዘ​መር፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ፥ አሕ​ዛብ ደነ​ገጡ፤ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መጠ፥ ምድ​ርን አነ​ዋ​ወ​ጣት።


ንጉ​ሡም ጸሓ​ፊ​ውን ባሮ​ክ​ንና ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ይይዙ ዘንድ የን​ጉ​ሡን ልጅ ይረ​ሕ​ም​ኤ​ል​ንና የዓ​ዝ​ር​ኤ​ልን ልጅ ሠራ​ያን የዓ​ብ​ድ​ኤ​ል​ንም ልጅ ሰሌ​ም​ያን አዘዘ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሰወ​ራ​ቸው።


እና​ንተ ፈጽ​ማ​ችሁ ሞታ​ች​ኋ​ልና፤ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ሠ​ወ​ረች ናትና።


በታላቅም ድምፅ እየጮሁ “ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የአምላካችንና የበጉ ነው!” አሉ።


በዚ​ያ​ችም ቀን ዲቦ​ራና የአ​ቢኒ​ሔም ልጅ ባርቅ እን​ዲህ ብለው ዘመሩ፦