Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 ሰማ​ያት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ይና​ገ​ራሉ፥ የሰ​ማ​ይም ጠፈር የእ​ጁን ሥራ ያወ​ራል።

2 ቀን ለቀን ነገ​ርን ታወ​ጣ​ለች፥ ሌሊ​ትም ለሌ​ሊት ጥበ​ብን ትና​ገ​ራ​ለች።

3 ቃላ​ቸው ያል​ተ​ሰ​ማ​በት ነገር የለም፥ መና​ገ​ርም የለም፥

4 ቃላ​ቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ። ነገ​ራ​ቸ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ።

5 በፀ​ሐይ ውስጥ ድን​ኳ​ኑን አደ​ረገ፥ እር​ሱም እንደ ሙሽራ ከእ​ል​ፍኙ ይወ​ጣል፤ በመ​ን​ገዱ እን​ደ​ሚ​ራ​መድ አር​በኛ ደስ ይለ​ዋል።

6 አወ​ጣጡ ከሰ​ማ​ያት ዳርቻ ነው፥ መግ​ቢ​ያ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ነው፤ ከት​ኩ​ሳ​ቱም የሚ​ሰ​ወር የለም።

7 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ንጹሕ ነው፤ ነፍ​ስ​ንም ይመ​ል​ሳል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር የታ​መነ ነው፤ ሕፃ​ና​ት​ንም ጠቢ​ባን ያደ​ር​ጋል።

8 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐት ቅን ነው፥ ልብ​ንም ደስ ያሰ​ኛል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ብሩህ ነው፥ ዐይ​ኖ​ች​ንም ያበ​ራል።

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ንጹሕ ነው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይኖ​ራል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ እው​ነ​ትና ቅን​ነት በአ​ን​ድ​ነት ነው።

10 ከወ​ር​ቅና ከክ​ቡር ዕንቍ ይልቅ ይወ​ደ​ዳል፤ ከማ​ርና ከማር ወለ​ላም ይልቅ ይጣ​ፍ​ጣል።

11 ባሪ​ያህ ደግሞ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፤ በመ​ጠ​በ​ቁም ብዙ ዋጋ ይቀ​በ​ላል።

12 ስሕ​ተ​ትን ማን ያስ​ተ​ው​ላ​ታል? ከተ​ሰ​ወረ ኀጢ​አቴ አን​ጻኝ።

13 ከልዩ ሰው ባሪ​ያ​ህን አድ​ነው። ካል​ገ​ዙኝ የዚ​ያን ጊዜ ፍጹም እሆ​ና​ለሁ፥ ከታ​ላ​ቁም ኀጢ​አቴ እነ​ጻ​ለሁ።

14 የአ​ን​ደ​በቴ ቃል ያማረ ይሁን፤ የልቤ ዐሳ​ብም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነው አቤቱ ረድ​ኤቴ መድ​ኀ​ኒ​ቴም።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች