Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በዋ​ሽ​ንት የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 አቤቱ፥ ቃሌን አድ​ምጥ፥ ጩኸ​ቴ​ንም አስ​ተ​ውል፤

2 የል​መ​ና​ዬን ቃል አድ​ምጥ፥ ንጉ​ሤና አም​ላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸ​ል​ያ​ለ​ሁና።

3 በማ​ለዳ ቃሌን ስማኝ፥ በማ​ለዳ በፊ​ትህ እቆ​ማ​ለሁ፥ እገ​ለ​ጥ​ል​ሃ​ለ​ሁም።

4 አንተ በደ​ልን የሚ​ወ​ድድ አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ህ​ምና፤ ክፉ​ዎች ከአ​ንተ ጋር አያ​ድ​ሩም።

5 ዐመ​ፀ​ኞ​ችም በዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት አይ​ኖ​ሩም፤ ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ ጠላህ።

6 ሐሰ​ትን የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ሁሉ ትጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ደም አፍ​ሳ​ሹ​ንና ሸን​ጋ​ዩን ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​የ​ፋል።

7 እኔ ግን በም​ሕ​ረ​ትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገ​ባ​ለሁ፤ አን​ተን በመ​ፍ​ራት በቤተ መቅ​ደ​ስህ እሰ​ግ​ዳ​ለሁ።

8 አቤቱ፥ በጽ​ድ​ቅህ ምራኝ፤ ስለ ጠላ​ቶቼ መን​ገ​ዴን በፊ​ትህ አቅና።

9 በአ​ፋ​ቸው እው​ነት የለ​ምና፥ ልባ​ቸ​ውም ከንቱ ነው፥ ጕሮ​ሮ​ኣ​ቸው እንደ ተከ​ፈተ መቃ​ብር ነው፤ በም​ላ​ሳ​ቸው ይሸ​ነ​ግ​ላሉ።

10 አቤቱ፥ ፍረ​ድ​ባ​ቸው፥ በነ​ገረ ሠሪ​ነ​ታ​ቸ​ውም ይው​ደቁ፤ እንደ ሐሰ​ታ​ቸ​ውም ብዛት አሳ​ድ​ዳ​ቸው፥ አቤቱ፥ እነ​ርሱ አሳ​ዝ​ነ​ው​ሃ​ልና።

11 በአ​ንተ የሚ​ታ​መ​ኑት ሁሉ ግን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ በእ​ነ​ር​ሱም ታድ​ራ​ለህ። ስም​ህ​ንም የሚ​ወ​ድዱ ሁሉ በአ​ንተ ይመ​ካሉ።

12 አንተ ጻድ​ቁን ትባ​ር​ከ​ዋ​ለ​ህና፤ አቤቱ፥ እንደ አላ​ባሽ ጋሻ ከለ​ል​ኸን።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች