የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 143:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አፋ​ቸው ከንቱ ነገ​ርን ከሚ​ና​ገር፥ ቀኛ​ቸ​ውም የዐ​መፃ ቀኝ ከሆነ አስ​ጥ​ለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በአንተ ታምኛለሁና፣ በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና፣ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ጽኑ ፍቅርህን አሰማኝ፥ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አሳውቀኝ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የምተማመነው በአንተ ስለ ሆነ በየጠዋቱ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ ሕይወቴን በዐደራ ለአንተ ስለ ሰጠሁ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 143:8
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለነ​ገ​ሥ​ታት መድ​ኀ​ኒ​ትን የሚ​ሰጥ፥ ባሪ​ያው ዳዊ​ትን ከክፉ ጦር የሚ​ያ​ድ​ነው እርሱ ነው።


በእ​ጅህ ነፍ​ሴን አደራ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የጽ​ድቅ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ተቤ​ዠኝ።


ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈ​ራ​ዋ​ለች፥ በዓ​ለም የሚ​ኖሩ ሁሉም ከእ​ርሱ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ል​ልታ፥ ጌታ​ች​ንም በመ​ለ​ከት ድምፅ ዐረገ።


አቤቱ፥ በጽ​ድ​ቅህ ምራኝ፤ ስለ ጠላ​ቶቼ መን​ገ​ዴን በፊ​ትህ አቅና።


የሚ​ያ​ው​ቁ​ኝን ረዓ​ብ​ንና ባቢ​ሎ​ንን አስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነሆ፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን፥ ጢሮ​ስም የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ሕዝብ፥ እነ​ዚህ በዚያ ተወ​ለዱ።


በእኔ ተማ​ም​ኖ​አ​ልና አድ​ነ​ዋ​ለሁ ስሜ​ንም አው​ቆ​አ​ልና እጋ​ር​ደ​ዋ​ለሁ።


ወደ ቀኝም ቢሆን ወደ ግራም ቢሆን በኋ​ላህ በዚህ መን​ገድ እን​ሂድ የሚ​ሉና የሚ​ሳ​ሳቱ ሰዎ​ችን ድምፅ ጆሮ​ዎ​ችህ ይሰ​ማሉ።


ታዳ​ጊህ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ የሚ​ረ​ባ​ህን ነገር የማ​ስ​ተ​ም​ርህ የም​ት​ሄ​ድ​ባ​ት​ንም መን​ገድ እን​ዴት እን​ደ​ም​ታ​ገኝ የም​መ​ራህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


ልባ​ች​ንን ከእ​ጃ​ችን ጋር ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰማይ እና​ንሣ።


እን​ወ​ቀው፤ እና​ው​ቀ​ውም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ከ​ተል፤ እንደ ወገ​ግ​ታም ተዘ​ጋ​ጅቶ እና​ገ​ኘ​ዋ​ለን፤ በም​ድ​ርም ላይ እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውና እንደ ኋለ​ኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመ​ጣል።


ማኑ​ሄም፥ “እነሆ፥ ቃልህ በደ​ረሰ ጊዜ የልጁ ነገሩ፥ ግብ​ሩስ ምን​ድን ነው?” አለው።


ዳዊ​ትም፥ “የቂ​አላ ሰዎች እኔ​ንና ሰዎ​ቼን በሳ​ኦል እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ና​ልን?” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል” ብሎ ተና​ገረ።