Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የቆሬ ልጆች መዝ​ሙር።

1 አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ እጆ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ብ​ጭቡ፥ በደ​ስታ ቃልም ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ።

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልዑል፥ ግሩ​ምም ነውና፥ በም​ድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።

3 አሕ​ዛ​ብን ከእኛ በታች፥ ወገ​ኖ​ች​ንም ከእ​ግ​ራ​ችን በታች አስ​ገ​ዛ​ልን።

4 ለር​ስቱ እኛን መረ​ጠን፥ የያ​ዕ​ቆ​ብን ውበት የወ​ደደ።

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ል​ልታ፥ ጌታ​ች​ንም በመ​ለ​ከት ድምፅ ዐረገ።

6 ዘምሩ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለን​ጉ​ሣ​ችን ዘምሩ።

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማ​ስ​ተ​ዋል ዘምሩ፤

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ላይ ነገሠ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ዱስ ዙፋኑ ላይ ይቀ​መ​ጣል።

9 የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች ከአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ጋር ተሰ​በ​ሰቡ፤ የም​ድር ኀይ​ለ​ኞች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ ብለ​ዋ​ልና።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች