Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ሰቈቃወ 3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ቅጣት፥ ንስ​ሓና ተስፋ

1 አሌፍ። በቍ​ጣው በትር ችግር ያየ ሰው እኔ ነኝ።

2 ብር​ሃን ወደ​ሌ​ለ​በት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰ​ደኝ።

3 ዘወ​ትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ።

4 ቤት። ሥጋ​ዬ​ንና ቁር​በ​ቴን አስ​ረጀ፥ አጥ​ን​ቴን ሰበረ።

5 በዙ​ሪ​ያዬ ቅጥር ሠራ​ብኝ፤ የመ​ከ​ራ​ው​ንም ጎዳና በእኔ ላይ አቀና።

6 እንደ ቀድሞ ሙታን በጨ​ለማ አኖ​ረኝ።

7 ጋሜል። እን​ዳ​ል​ወጣ በዙ​ሪ​ያዬ ቅጥር ሠራ​ብኝ፤ ሰን​ሰ​ለ​ቴ​ንም አከ​በደ።

8 በጠ​ራ​ሁና በጮ​ኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ተከ​ለ​ከለ።

9 መን​ገ​ዴን በዓ​ለት ላይ ሠራ፤ ጎዳ​ና​ዬ​ንም አጠረ።

10 ዳሌጥ። እን​ደ​ም​ት​ሸ​ምቅ ድብ እንደ ተሸ​ሸ​ገም አን​በሳ ሆነ​ብኝ።

11 ተከ​ተ​ለኝ፤ ጨረ​ሰኝ፤ ባድ​ማም አደ​ረ​ገኝ።

12 ቀስ​ቱን ገተረ፤ ለፍ​ላ​ጻ​ውም እንደ ዒላማ አደ​ረ​ገኝ።

13 ሄ። የሰ​ገ​ባ​ውን ፍላ​ጻ​ዎች በኵ​ላ​ሊቴ ውስጥ ተከለ።

14 ለወ​ገኔ ሁሉ መሳ​ቂያ ሆንሁ፤ ቀኑ​ንም ሁሉ ዘፈ​ኑ​ብኝ።

15 ምሬ​ትን አጠ​ገ​በኝ፤ በሐ​ሞ​ትም አሰ​ከ​ረኝ።

16 ዋው። ጥር​ሴን በጭ​ንጫ ሰበረ፤ አመ​ድም አቃ​መኝ።

17 ነፍ​ሴን ከሰ​ላም አራቀ፤ በጎ ነገ​ርን ረሳሁ።

18 እኔም፦ ኀይ​ሌን፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ያለ​ውን ተስ​ፋ​ዬን አጣሁ።

19 ዛይ። ስደ​ቴ​ንና ችግ​ሬን፥ እሬ​ት​ንና ሐሞ​ትን አስብ።

20 ነፍሴ እያ​ሰ​በ​ችው በው​ስጤ ፈዘ​ዘች።

21 ይህ​ችን በልቤ አኖ​ራ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ እታ​ገ​ሣ​ለሁ።

22 ሔት። ያል​ጠ​ፋ​ነው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት የተ​ነሣ ነው፤ ርኅ​ራ​ኄው አያ​ል​ቅ​ምና።

23 ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማ​ኝ​ነ​ትህ ብዙ ነው።

24 ነፍሴ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እድል ፋን​ታዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ጠበ​ቅ​ሁት” አለች።

25 ጤት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ታ​ገ​ሡት ቸር ነው፤

26 ለም​ት​ሻ​ውና ለም​ት​ታ​ገሥ፥ ዝም ብላም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን ተስፋ ለም​ታ​ደ​ርግ ነፍስ መል​ካም ነው።

27 ሰው በታ​ና​ሽ​ነቱ ቀን​በር ቢሸ​ከም መል​ካም ነው።

28 ዮድ። እርሱ አሸ​ክ​ሞ​ታ​ልና ዝም ብሎ ለብ​ቻው ይቀ​መጥ።

29 ተስፋ ይሆ​ነው እንደ ሆነ አፉን በአ​ፈር ውስጥ ያኑር።

30 ጕን​ጩን ለሚ​መ​ታው ይሰ​ጣል፤ ስድ​ብ​ንም ይጠ​ግ​ባል።

31 ካፍ። ጌታ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጥ​ል​ምና፤

32 ያሳ​ዘ​ነ​ውን ሰው እንደ ይቅ​ር​ታው ብዛት ይም​ረ​ዋ​ልና፤

33 ከልቡ አል​ተ​ቈ​ጣ​ምና፥ የሰ​ው​ንም ልጆች አላ​ሳ​ዘ​ነ​ምና፥

34 ላሜድ። በም​ድር የተ​ጋ​ዙ​ትን ሁሉ ከእ​ግሩ በታች ይረ​ግ​ጣ​ቸው ዘንድ፥

35 የሰ​ውን ፍርድ በል​ዑል ፊት ይመ​ልስ ዘንድ፥

36 በሚ​ፈ​ር​ድ​በት ጊዜ የሰ​ውን ፍርድ ያጣ​ምም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላ​ዘ​ዘም።

37 ሜም። “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ይመ​ጣል፥

38 ከል​ዑል አፍም ያል​ወጣ መል​ካም ወይም ክፉ ይሆ​ናል” የሚል ማን ነው?

39 ሰው ሕያው ሲሆን ስለ ኀጢ​አቱ ለምን ያጕ​ረ​መ​ር​ማል?

40 ኖን። መን​ገ​ዳ​ች​ንን እን​መ​ር​ም​ርና እን​ፈ​ትን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​መ​ለስ።

41 ልባ​ች​ንን ከእ​ጃ​ችን ጋር ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰማይ እና​ንሣ።

42 በድ​ለ​ናል፤ ዐም​ፀ​ና​ልም፤ አን​ተም አል​ራ​ራ​ህ​ል​ንም።

43 ሳም​ኬት። በቍ​ጣህ ከደ​ን​ኸን፤ አሳ​ደ​ድ​ኸ​ንም፤ ገደ​ል​ኸን፤ አል​ራ​ራ​ህ​ል​ንም።

44 ጸሎ​ታ​ችን እን​ዳ​ያ​ርግ ራስ​ህን በደ​መና ከደ​ንህ።

45 እን​ድ​ና​ዝ​ንና እን​ዳ​ና​ይም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አስ​ቀ​መ​ጥ​ኸን።

46 ዔ። ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ በእኛ ላይ አፋ​ቸ​ውን ከፈቱ።

47 ፍር​ሀ​ትና ቍጣ፥ ጥፋ​ትና ቅጥ​ቃጤ ያዘን።

48 ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥ​ቃጤ ከዐ​ይኔ የውኃ ጐርፍ ፈሰሰ።

49 ፌ። ዐይኔ ተደ​ፈ​ነች፤ እን​ግ​ዲህ ከማ​ን​ጋ​ጠጥ ዝም አል​ልም።

50 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሆኖ እስ​ኪ​መ​ለ​ከት ድረስ።

51 ስለ ከተ​ማዬ ቈነ​ጃ​ጅት ሁሉ ዐይኔ ነፍ​ሴን አሳ​ዘ​ነች።

52 ጻዴ። በከ​ንቱ ነገር ጠላ​ቶች ሁሉ እንደ ወፍ ማደ​ንን አደ​ኑኝ።

53 ጠላ​ቶች ሕይ​ወ​ቴን በጕ​ድ​ጓድ አጠፉ፤ በላ​ዬም ድን​ጋይ ገጠሙ።

54 በራሴ ላይ ውኃ ተከ​ነ​በለ፤ እኔም፥ “ጠፋሁ” ብዬ ነበር።

55 ቆፍ። አቤቱ፥ በጥ​ልቅ ጕድ​ጓድ ውስጥ ሆኜ ስም​ህን ጠራሁ።

56 አንተ ድም​ፄን ሰማህ፤ ጆሮ​ህ​ንም ከል​መ​ናዬ አት​መ​ልስ።

57 በጠ​ራ​ሁህ ቀን ወደ እኔ ቅረብ፤ “አት​ፍ​ራም” በለኝ።

58 ሬስ። አቤቱ፥ የነ​ፍ​ሴን ፍርድ ፈረ​ድህ፤ ሕይ​ወ​ቴ​ንም ተቤ​ዥህ።

59 አቤቱ፥ ጭን​ቀ​ቴን አይ​ተ​ሃል፤ ፍር​ዴን ፍረ​ድ​ልኝ።

60 በቀ​ላ​ቸ​ውን ሁሉና በእኔ ላይ ያለ​ውን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሁሉ አየህ።

61 ሣን። አቤቱ፥ ስድ​ባ​ቸ​ው​ንና በእኔ ላይ ያለ​ውን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሁሉ ሰማህ።

62 የተ​ነ​ሡ​ብ​ኝን ሰዎች ከን​ፈ​ሮች ቀኑ​ንም ሁሉ ያሰ​ቡ​ብ​ኝን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሰማህ።

63 መቀ​መ​ጣ​ቸ​ው​ንና መነ​ሣ​ታ​ቸ​ውን ተመ​ል​ከት፤ እኔ መዝ​ፈ​ኛ​ቸው ነኝ።

64 ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃ​ቸው ሥራ ፍዳ​ቸ​ውን ክፈ​ላ​ቸው።

65 የልብ ሕማ​ም​ንና ርግ​ማ​ን​ህን ስጣ​ቸው።

66 አቤቱ፥ እንደ ልባ​ቸው ክፋት በቍ​ጣህ ታሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ማ​ይም በታች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች