መዝሙር 86 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር። 1 መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤ 2 ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል። 3 የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ የተነገረው ነገር ድንቅ ነው። 4 የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ፤ እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን፥ ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ፥ እነዚህ በዚያ ተወለዱ። 5 ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት። 6 እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል። 7 በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል። |