የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡ​ትን ሁሉ፥ አን​ተና አሮን በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ቍጠ​ሩ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በመላው እስራኤል ያሉትን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያም በላይ ሆኖ ለውጊያ ብቁ የሆኑትን ወንዶች ሁሉ አንተና አሮን በየምድባቸው ቍጠሯቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን፥ ከእስራኤል ወደ ጦርነት የሚወጣውን ሁሉ፥ አንተና አሮን በየሠራዊቶቻቸው ቁጠሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን፥ ከእስራኤል ወደ ሰልፍ የሚወጡትን ሁሉ፥ አንተና አሮን በየሠራዊቶቻቸው ቍጠሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 1:3
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮ​አ​ብም የሕ​ዝ​ቡን ቍጥር ድምር ለን​ጉሡ ሰጠ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ስም​ንት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ሰዎች ነበሩ፤ የይ​ሁ​ዳም ተዋ​ጊ​ዎች ሰዎች አም​ስት መቶ ሺህ ነበሩ።


የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥ ጽኑ​ዓን ጋሻና ሰይፍ የሚ​ይዙ፥ ቀስ​ተ​ኞ​ችም፥ ሰልፍ የሚ​ያ​ውቁ ሰል​ፈ​ኞ​ችም፥ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ።


ንጉሡ አሜ​ስ​ያ​ስም የይ​ሁ​ዳን ሕዝብ ሰበ​ሰበ፤ እንደ እየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አቆ​ማ​ቸው፤ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሁሉ የሽህ አለ​ቆ​ች​ንና የመቶ አለ​ቆ​ችን አደ​ረገ፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ​ትን ሁሉ ቈጠረ፤ ለሰ​ል​ፍም የሚ​ወጡ፥ ጋሻና ጦርም የሚ​ይዙ ሦስት መቶ ሺህ የተ​መ​ረጡ ሰዎ​ችን አገኘ።


በዚ​ህም ቀን ሠራ​ዊ​ታ​ች​ሁን ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ዋ​ለ​ሁና ይህን ትእ​ዛዝ ጠብ​ቁት፤ እን​ግ​ዲህ ይህን ቀን ለልጅ ልጃ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት አድ​ር​ጋ​ችሁ ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ።


ይቈ​ጠር ዘንድ የሚ​ያ​ል​ፈው ሁሉ፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም ከፍ ያለ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦታ ይሰ​ጣል።


እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው አንድ አንድ ዲድ​ር​ክም አዋጣ፤ አንድ ዲድ​ር​ክም እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን የሰ​ቅል ግማሽ ነው፤ ይህም የተ​ዋ​ጣው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ከተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበረ።


በድ​ኖ​ቻ​ችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የተ​ቈ​ጠ​ራ​ችሁ ሁሉ፥ እንደ ቍጥ​ራ​ችሁ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እና​ንተ ያጕ​ረ​መ​ረ​ማ​ች​ሁ​ብኝ፥


“ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጣ​ውን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ቍጠሩ።”


“የሌ​ዊን ልጆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ቍጠር፤ ወን​ዱን ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ቍጠ​ራ​ቸው።”


ከግ​ብፅ የወ​ጡት ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ውቁ ሰዎች እኔን ፈጽ​መው አል​ተ​ከ​ተ​ሉ​ምና ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እሰጥ ዘንድ የማ​ል​ሁ​ባ​ትን ምድር አያ​ዩም፤


በሙ​ሴና በአ​ሮን እጅ ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሰ​ፈ​ሩ​በት ይህ ነው።


ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​በ​ትን ሁሉ ትለ​ያ​ለህ።


“አዲስ ሚስ​ትም ያገባ ሰው ወደ ጦር​ነት አይ​ሂድ፤ ምንም ነገር አይ​ጫ​ኑ​በት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በቤቱ በፈ​ቃዱ ይቀ​መጥ፤ የወ​ሰ​ዳ​ት​ንም ሚስ​ቱን ደስ ያሰ​ኛት።


“በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ኋ​ችሁ፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ምድር ርስት አድ​ርጎ ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን ይዛ​ችሁ እና​ንተ አር​በ​ኞች ሁሉ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ።