ዘኍል 33:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 በሙሴና በአሮን እጅ ከሠራዊቶቻቸው ጋር ከግብፅ ከወጡ በኋላ የእስራኤል ልጆች የሰፈሩበት ይህ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ወጥተው፣ በጕዞ ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 በሙሴና በአሮን ልጅ እየተመሩ በየሠራዊታቸው ሆነው ከግብጽ በወጡ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ያደረጉት ጉዞ ይህ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ከወጡ በኋላ በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች የሚያስረዳው ታሪክ ይህ ነው፦ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን ልጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ በወጡ ጊዜ እንዲህ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |