Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 33:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሙሴና በአሮን ልጅ እየተመሩ በየሠራዊታቸው ሆነው ከግብጽ በወጡ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ያደረጉት ጉዞ ይህ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ወጥተው፣ በጕዞ ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ከወጡ በኋላ በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች የሚያስረዳው ታሪክ ይህ ነው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በሙ​ሴና በአ​ሮን እጅ ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሰ​ፈ​ሩ​በት ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን ልጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ በወጡ ጊዜ እንዲህ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 33:1
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አገልጋዩን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ።


መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፥ ያለፍከውም ኃይለኛ ውኆች በኩል ነው፤ ዱካህ ግን አልታወቀም።


የእስራኤልም ልጆች ከራዓምሴስ ወደ ሱኮት በእግር ተጓዙ፤ ከሕፃናቱም ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህሉ ነበሩ።


እንዲህም ሆነ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ በዚህ ቀን የጌታ ሠራዊት ሁሉ ከግብጽ ምድር ወጡ።


በዚያም ቀን ጌታ የእስራኤልን ልጆች ከሠራዊታቸው ጋር ከግብጽ ምድር አወጣ።


ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን ዞረው በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መንገድ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች ከግብጽ ምድር ለጦርነት ተሰልፈው ወጡ።


እነዚህ አሮንና ሙሴ ጌታ፦ “የእስራኤልን ልጆች በየነገዳቸው ከግብጽ ምድር አውጡ” ያላቸው ናቸው።


ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁና፤ በፊትህም ሙሴን፥ አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።


ሙሴም በጌታ ትእዛዝ የጉዞአቸው መነሻ የሆኑትን ስፍራዎቻቸውን ጻፈ፤ እንደ መነሻ ስፍራዎቻቸው ጉዞአቸው እንዲህ ነበረ።


ሙሴንና አሮንንም ላክሁ፥ በመካከላቸውም እንዳደረግሁ ግብጽን ቀሠፍሁ፤ ከዚያም በኋላ እናንተን አወጣሁ።


ያዕቆብ ወደ ግብጽ ከገባ በኋላ፥ አባቶቻችሁ ጌታ እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ጮኹ፤ ጌታም የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲኖሩ ያደረጉትን ሙሴንና አሮንን ላከላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች