Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 32:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከግ​ብፅ የወ​ጡት ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ውቁ ሰዎች እኔን ፈጽ​መው አል​ተ​ከ​ተ​ሉ​ምና ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እሰጥ ዘንድ የማ​ል​ሁ​ባ​ትን ምድር አያ​ዩም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ‘በፍጹም ልባቸው ስላልተከተሉኝ ከግብጽ ከወጡት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች አንዳቸውም ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ ልሰጥ በመሐላ ቃል የገባሁላቸውን ምድር አያዩዋትም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ‘ከግብጽ የወጡት ዕድሜአቸው ሀያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያም በላይ ያሉት ሰዎች እኔን ፈጽመው አልተከተሉምና ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ለመስጠት የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11-12 እርሱም፦ በእውነት እግዚአብሔርን ፈጽመው ከተከተሉ ከእነዚህ ከቄኔዛዊው ከዮፎኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር፥ ከግብፅ የወጡት ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት ሰዎች እኔን ፈጽመው አልተከተሉምና ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እሰጥ ዘንድ የማልሁበትን ምድር አያዩም ብሎ ማለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 32:11
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእ​ው​ነት ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር አያ​ዩም፤ ከእኔ ጋር በዚህ ላሉ መል​ካ​ም​ንና ክፉን ለይ​ተው ለማ​ያ​ውቁ ልጆ​ቻ​ቸው፥ የሚ​ያ​ው​ቀው ለሌለ ለታ​ናሹ ሁሉ ያችን ሀገር እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለጥ​ፋት ያነ​ሳ​ሱኝ ሁሉ አያ​ዩ​አ​ትም።


ወዳጄ ካሌብ ግን ሌላ መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ ስለ ሆነና ስለ ተከ​ተ​ለኝ እርሱ ወደ ገባ​ባት ምድር አገ​ባ​ዋ​ለሁ፤ ዘሩም ይወ​ር​ሳ​ታል።


“ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጣ​ውን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ቍጠሩ።”


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ እሰ​ጣት ዘንድ የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር ከእ​ነ​ዚህ ሰዎች ማንም አያ​ይም፥


እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ግቡ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ርሱ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለዘ​ራ​ቸው ይሰ​ጣት ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ውረሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች