Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 14:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 በድ​ኖ​ቻ​ችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የተ​ቈ​ጠ​ራ​ችሁ ሁሉ፥ እንደ ቍጥ​ራ​ችሁ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እና​ንተ ያጕ​ረ​መ​ረ​ማ​ች​ሁ​ብኝ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 በተደረገው ቈጠራ መሠረት፣ ሃያ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆናችሁና በእኔም ላይ ያጕረመረማችሁ ሁሉ በድናችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ፤ ከአጠቃላይም ቁጥራችሁ፥ በእኔ ላይ ያጉረመረሙ ዕድሜአቸው ሀያ ዓመት የሆናቸውና ከዚያም በላይ ሆነው የተቈጠሩት ሁሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ሁላችሁም ትሞታላችሁ፤ ሬሳችሁም በዚህ ምድረ በዳ ተበትኖ ይቀራል፤ በእኔ ላይ በማጒረምረማችሁ ምክንያት ከእናንተ መካከል ከኻያ ዓመት በላይ ዕድሜ ኖሮአችሁ የተቈጠራችሁት ሁሉ ከቶ ወደዚያች ምድር አትገቡም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ፤ የተቈጠራችሁ ሁሉ፥ እንደ ቍጥራችሁ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እናንተ ያጕረመረማችሁብኝ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 14:29
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ሰማይ ይወ​ጣሉ፥ ወደ ጥል​ቅም ይወ​ር​ዳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም በመ​ከራ ቀለ​ጠች።


ከእ​ና​ን​ተም ዘንድ ዐመ​ፀ​ኞ​ች​ንና የበ​ደ​ሉ​ኝን እለ​ያ​ለሁ፤ ከኖ​ሩ​ባ​ትም ምድር አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር ግን አይ​ገ​ቡም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ነገድ ከየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አንድ አንድ አለቃ ነበረ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁሉ፥ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥


የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።


ነገር ግን ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው ጊዜ ከነ​በ​ሩት ከእ​ነ​ዚያ መካ​ከል አን​ድም ሰው አል​ነ​በ​ረም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ፥ “በእ​ው​ነት በም​ድረ በዳ ይሞ​ታሉ” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና። ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ፥ ከነ​ዌም ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው ስንኳ አል​ቀ​ረም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከእ​ነ​ርሱ በሁ​ሉም ደስ አላ​ለ​ውም፤ ብዙ​ዎቹ በም​ድረ በዳ ወድ​ቀ​ዋ​ልና።


የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ እስከ ተሻ​ገ​ር​ን​በት ድረስ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማለ​ባ​ቸው ተዋ​ጊ​ዎች የሆኑ የዚ​ያች ትው​ልድ ሰዎች ከሰ​ፈሩ መካ​ከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃ​ዴስ በርኔ የተ​ጓ​ዝ​ን​በት ዘመን ሠላሳ ስም​ንት ዓመት ሆነ።


አርባ ዘመን የተ​ቈ​ጣ​ቸ​ውስ እነ​ማን ነበሩ? የበ​ደሉ፥ ሬሳ​ቸ​ውም በም​ድረ በዳ የወ​ደ​ቀው አይ​ደ​ሉ​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ለእኛ ይሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር እን​ደ​ማ​ያ​ሳ​ያ​ቸው የማ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ከግ​ብፅ የወጡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያል​ሰሙ፥ እነ​ዚያ ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አርባ ዓመት በመ​ድ​በራ ምድረ በዳ ይዞሩ ነበር።


ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች