ኢያሱ 12:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተራራና በሜዳ በዓረባ፥ በአሴዶት በቆላው፥ በናጌብ፥ በኬጤዎንና በአሞሬዎን፥ በከናኔዎንና በፌርዜዎን፥ በኢያቡሴዎንና በኤዌዎን ያለ ርስታቸውን አወረሳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ተራራማው አገር፤ በስተምዕራብ ያለው የኰረብታ ግርጌ፣ ዓረባ፣ የተራራው ሸንተረሮች፣ ምድረ በዳውና ኔጌብ ማለት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው። ነገሥታቱም እነዚህ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተራራማው አገር፥ በቈላውም፥ በዓረባም፥ በቁልቁለቱም፥ በምድረ በዳውም፥ በደቡቡም ያሉ ኬጢያውያን አሞራውያንም ከነዓናውያንም ፌርዛውያንም ኤዊያውያንም ኢያቡሳውያንም ዘንድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የርስት ድርሻ ኮረብታማውን አገር በስተ ምዕራብ ያለውን የኮረብታ ግርጌ፥ የዮርዳኖስን ሸለቆና በእርሱም ኮረብታዎች ግርጌ ያሉትን በስተ ምሥራቅ በኩል የሚገኘውን ረባዳ ቦታና በደቡብ በኩል የሚገኘውን በረሓማ ምድር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ ይህም ምድር ቀድሞ የሒታውያን፥ የአሞራውያን፥ የከነዓናውያን፥ የፈሪዛውያን፥ የሒዋውያንና የኢያቡሳውያን መኖሪያ ነበር። |
በአብራምና በሎጥ መንጎች ጠባቆች መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።
መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ያገባሃል፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ።
ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም ሀገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊዪቱና ወደ መልካሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
“አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከፊትህም ብዙና ታላላቅ አሕዛብን፥ ከአንተ የበለጡትን፥ የበረቱትንም ሰባቱን አሕዛብ፥ ኬጤዎናዊውን፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ከነዓናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ባወጣ ጊዜ፥
“እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ከአንተ የበለጡትንና የበረቱትን አሕዛብ፥ የቅጽራቸው ግንብ እስከ ሰማይ የሚደርስ ታላላቆች ከተሞችን ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገረዋለህ።
እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ፥ ተራራማውን ሀገር፥ ደቡቡንም፥ ቆላውንም፥ ቍልቍለቱንም፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ መታ፤ ማንንም አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
ኢያሱም ያን ምድር ሁሉ፥ ተራራማውን፥ ደቡቡንም ሁሉ፥ የጎሶምንም ምድር ሁሉ ፥ ሜዳውንም፥ በምዕራብ በኩል ያለውንም፥ የእስራኤልንም ተራራማውንና ቆላውን ያዘ፤
ኢያሱም አለ፥ “ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነ፥ እርሱም ከፊታችሁ ከነዓናዊውን፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ፈጽሞ እንዲያጠፋቸው በዚህ ታውቃላችሁ።
እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማው በሜዳውም በታላቁ ባሕር ዳር በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥት ሁሉ፥ ኬጤዎናዊዉ፥ አሞሬዎናዊዉም፥ ከነዓናዊዉም፥ ፌርዜዎናዊዉም፥ ኤዌዎናዊዉም፥ ኢያቡሴዎናዊዉም፥ ጌርጌሴዎናዊዉም ይህን በሰሙ ጊዜ፥
ከዚያም በኋላ የይሁዳ ልጆች በተራራማው ሀገርና በደቡብ በኩል በቈላው ውስጥ የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ሊወጉ ወረዱ።