Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ኢያሱ 12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሙሴ ድል ያደ​ረ​ጋ​ቸው ነገ​ሥት

1 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የመ​ቱ​አ​ቸው፥ ከአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አር​ሞ​ን​ዔም ተራራ ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል ያለ​ውን ዓረባ ሁሉ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ በፀ​ሐይ መውጫ ያለ​ውን ሀገ​ራ​ቸ​ውን የወ​ረ​ሱ​አ​ቸው የም​ድር ነገ​ሥት እነ​ዚህ ናቸው፤

2 በሐ​ሴ​ቦን የተ​ቀ​መ​ጠው፥ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ ከሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን እኩ​ሌታ እስከ ኢያ​ቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፤

3 በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ያለ​ውን ዓረባ እስከ ኬኔ​ሬት ባሕር ድረስ፥ በአ​ሴ​ሞት መን​ገድ አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ከፋ​ስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለ​ውን ምድር የገ​ዛው የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ ሴዎን፤

4 ከረ​ዓ​ይት ወገን የቀረ፥ በአ​ስ​ጣ​ሮ​ትና በኤ​ን​ድ​ራ​ይን የተ​ቀ​መ​ጠው፥

5 የአ​ር​ሞ​ን​ኤ​ምን ተራራ፥ ካሴ​ኪን፥ ባሳ​ን​ንም ሁሉ እስከ ጌር​ጌ​ሲና እስከ መከጢ ዳርቻ፥ የገ​ለ​ዓ​ድ​ንም እኩ​ሌታ እስከ ሐሴ​ቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገ​ዛው የባ​ሳን ንጉሥ ዐግ፤

6 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ ርስት አድ​ርጎ ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለጋ​ድም ልጆች፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው።


ኢያሱ ድል ያደ​ረ​ጋ​ቸው ነገ​ሥት

7 የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና ኢያሱ በሊ​ባ​ኖስ ቆላ፥ በበ​ላ​ጋድ ባሕር፥ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሴይር በሚ​ደ​ርስ በኬ​ልኪ ተራራ የገ​ደ​ሉ​አ​ቸው የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥት እነ​ዚህ ናቸው። ኢያ​ሱም ያችን ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሰጣ​ቸው።

8 በተ​ራ​ራና በሜዳ በዓ​ረባ፥ በአ​ሴ​ዶት በቆ​ላው፥ በና​ጌብ፥ በኬ​ጤ​ዎ​ንና በአ​ሞ​ሬ​ዎን፥ በከ​ና​ኔ​ዎ​ንና በፌ​ር​ዜ​ዎን፥ በኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ንና በኤ​ዌ​ዎን ያለ ርስ​ታ​ቸ​ውን አወ​ረ​ሳ​ቸው።

9 የኢ​ያ​ሪኮ ንጉሥ፥ በቤ​ቴል አጠ​ገብ ያለ​ችው የጋይ ንጉሥ፥

10 የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ፥ የኬ​ብ​ሮን ንጉሥ፥

11 የኢ​ያ​ሪ​ሙት ንጉሥ፥ የለ​ኪስ ንጉሥ፥

12 የኤ​ላም ንጉሥ፥ የጋ​ዜር ንጉሥ፥

13 የዳ​ቤር ንጉሥ፥ የጋሴ ንጉሥ፥

14 የኤ​ር​ሞት ንጉሥ፥ የዓ​ራድ ንጉሥ፥

15 የል​ብና ንጉሥ፥ የዓ​ዶ​ላም ንጉሥ፥

16 የመ​ቄዳ ንጉሥ፥

17 የኤ​ጣ​ፋድ ንጉሥ፥

18 የኦ​ፌር ንጉሥ፥

19 የአ​ፌ​ጠ​ቀ​ሰ​ሩት ንጉሥ፥ የአ​ሶር ንጉሥ፥

20 የስ​ሚ​ዖን ንጉሥ፥ የመ​ም​ሮት ንጉሥ፥

21 የአ​ዚፍ ንጉሥ፥ የቃ​ዴስ ንጉሥ፥

22 የዘ​ቃክ ንጉሥ፥ የማ​ር​ዶት ንጉሥ፥ በቀ​ር​ሜ​ሎስ የነ​በረ የዴ​ቆም ንጉሥ፥

23 በፌ​ና​ድር ክፍል የም​ት​ሆን የኤ​ዶር ንጉሥ፥ በጋ​ልያ ክፍል የም​ት​ሆን የሐጌ ንጉሥ፥ የቲ​ርሣ ንጉሥ፥

24 እነ​ዚህ ነገ​ሥት ሁሉ ሃያ ዘጠኝናቸው።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች