Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ኢያሱ 11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ኢያሱ ኢያ​ቢ​ስ​ንና ሌሎች ነገ​ሥ​ታ​ትን ድል እን​ዳ​ደ​ረገ

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የአ​ሶር ንጉሥ ኢያ​ቢስ ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ማሮን ንጉሥ ወደ ዮባብ፥ ወደ ስሚ​ዖን ንጉሥ፥ ወደ አዚ​ፍም ንጉሥ፥

2 በመ​ስ​ዕም በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ፥ በከ​ነ​ሬ​ትም ዐዜብ በዓ​ረባ፥ በቆ​ላ​ውም ባለ በፊ​ና​ዶር ሸለቆ ወደ ነበሩ ነገ​ሥ​ታት፥

3 በም​ሥ​ራ​ቃዊ ባሕር ዳርቻ ወዳ​ለው ወደ ከነ​ዓ​ና​ዊው፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ውም፥ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር ወዳ​ለው ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊው፥ በቆ​ላ​ማ​ውና በመ​ሴፋ ወዳ​ለው ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ዉም ላከ።

4 እነ​ርሱ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ብዛ​ታ​ቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆነው ወጡ፤ ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎ​ችም እጅግ ብዙ​ዎች ነበሩ።

5 እነ​ዚ​ህም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በማ​ሮን ውኃ አጠ​ገብ አንድ ሆነው ተያ​ያ​ዙ​አ​ቸው።

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን ቋንጃ ትቈ​ር​ጣ​ለህ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ” አለው።

7 ኢያ​ሱና ተዋ​ጊ​ዎች ሕዝ​ብም ሁሉ በድ​ን​ገት ወደ ማሮን ውኃ መጡ​ባ​ቸው፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ቦታ ወደ​ቁ​ባ​ቸው።

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ መቱ​አ​ቸ​ውም፤ ወደ ታላ​ቂ​ቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴ​ሮ​ንም፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወዳ​ለው ወደ ሞሳሕ ሸለቆ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ማን​ንም ሳያ​ስ​ቀሩ መቱ​አ​ቸው።

9 ኢያ​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቋንጃ ቈረጠ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠለ።

10 በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ኢያሱ ተመ​ልሶ አሶ​ርን ያዘ፤ ንጉ​ሥ​ዋ​ንም በሰ​ይፍ ገደለ፤ አሶ​ርም አስ​ቀ​ድሞ የእ​ነ​ዚህ መን​ግ​ሥ​ታት ዋና ከተማ ነበ​ረች።

11 በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ሰዎች ሁሉ በሰ​ይፍ ገደሉ፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ሳያ​ስ​ቀሩ ሁሉ​ንም አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ አሶ​ር​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ላት፤

12 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ ኢያሱ የእ​ነ​ዚ​ህን መን​ግ​ሥ​ታት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያዘ፤ በሰ​ይ​ፍም መታ​ቸው፤ ፈጽ​ሞም አጠ​ፋ​ቸው።

13 ከአ​ቃ​ጠ​ሏት ከአ​ሶር ብቻ በቀር እስ​ራ​ኤል በየ​አ​ው​ራ​ጃ​ቸው የነ​በ​ሩ​ትን ሌሎች ከተ​ሞች ሁሉ አላ​ቃ​ጠ​ሉም።

14 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የእ​ነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ምርኮ ሁሉ፥ ከብ​ቶ​ቹ​ንም ለራ​ሳ​ቸው ዘረፉ፤ ሰዎ​ቹን ሁሉ ግን እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያለ​ው​ንም ሁሉ አን​ድም አላ​ስ​ቀ​ሩም።

15 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዩን ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ ሙሴ ኢያ​ሱን አዝ​ዞት ነበር፤ ኢያ​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ካዘ​ዘው ሁሉ ምንም አላ​ስ​ቀ​ረም።


ኢያሱ ሌሎ​ችን ግዛ​ቶች እንደ ያዘ

16 ኢያ​ሱም ያን ምድር ሁሉ፥ ተራ​ራ​ማ​ውን፥ ደቡ​ቡ​ንም ሁሉ፥ የጎ​ሶ​ም​ንም ምድር ሁሉ ፥ ሜዳ​ው​ንም፥ በም​ዕ​ራብ በኩል ያለ​ው​ንም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ተራ​ራ​ማ​ው​ንና ቆላ​ውን ያዘ፤

17 እስከ ሴይ​ርም ከሚ​ያ​ወ​ጣው ከኤ​ኬል ተራራ ጀምሮ ከአ​ር​ሞ​ን​ዔም ተራራ በታች እስከ ሊባ​ኖስ ሜዳና እስከ በላ​ጋድ ድረስ፤ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ይዞ መታ​ቸው፤ ገደ​ላ​ቸ​ውም።

18 ኢያ​ሱም ብዙ ዘመን ከእ​ነ​ዚሁ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር።

19 በገ​ባ​ዖን ከሚ​ኖሩ ከኤ​ዎ​ና​ው​ያን በቀር፤ እስ​ራ​ኤል ያል​ያ​ዙት ከተማ አል​ነ​በ​ረም፥ ሁሉን በጦ​ር​ነት ያዙ።

20 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ፥ ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ይ​ራ​ሩ​ላ​ቸው ፈጽ​መው እን​ዲ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይጋ​ጠሙ ዘንድ ልባ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ደ​ነ​ድኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልባ​ቸ​ውን አጸና።

21 በዚያ ጊዜም ኢያሱ ሄደ፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር የሚ​ኖሩ ኤና​ቃ​ው​ያ​ንን ከኬ​ብ​ሮ​ንና ከዳ​ቤር፥ ከአ​ና​ቦ​ትም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራራ ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳም ተራራ ሁሉ አጠ​ፋ​ቸው፤ ኢያ​ሱም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ፈጽሞ አጠ​ፋ​ቸው።

22 በጋዛ፥ በጌ​ትም፥ በአ​ዛ​ጦ​ንም ከቀ​ሩት በቀር በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ከኤ​ና​ቃ​ው​ያን ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም።

23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ክፍ​ላ​ቸው በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱም ከጦ​ር​ነት ዐረ​ፈች።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች