ኢያሱ 12:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ልጆችና ኢያሱ በሊባኖስ ቆላ፥ በበላጋድ ባሕር፥ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሴይር በሚደርስ በኬልኪ ተራራ የገደሉአቸው የከነዓን ነገሥት እነዚህ ናቸው። ኢያሱም ያችን ምድር ለእስራኤል ወገኖች ሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ኢያሱና እስራኤላውያን ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ድል ያደረጓቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ ግዛታቸውም በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ ካለው ከበኣልጋድ ተነሥቶ በምዕራብ ሴይር እስካለው እስከ ሐላቅ ተራራ ይደርሳል፤ ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ምድር እንደ ነገዳቸው አከፋፈል ለእስራኤላውያን በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱና የእስራኤል ልጆች ያሸነፉአቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም የነበሩት በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል በሊባኖስ ሸለቆ ካለችው ከበኣልጋድ ወደ ሴይር ተራራ እስከሚያወጣው እስከ ሐላቅ ተራራ ድረስ ኢያሱ በየድርሻቸው ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገድ በሰጣት ምድር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ባለው ምድር የነበሩትን ነገሥታት ሁሉ ድል ነሡ፤ ይህም ምድር በሊባኖስ ሸለቆ ከሚገኘው ከባዓልጋድ ተነሥቶ በደቡብ በኩል በኤዶም አጠገብ እስካለው እስከ ሐላክ ተራራ ይደርስ ነበር፤ ኢያሱም ይህን ምድር በማከፋፈል ለእያንዳንዱ ነገድ ርስት አድርጎ ሰጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል በሊባኖስ ሸለቆ ካለችው ከበኣልጋድ ወደ ሴይር ተራራ እስከሚያወጣው ወና እስከ ሆነው ተራራ ድረስ ኢያሱ በየክፍላቸው ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገድ በሰጣት ምድር፥ በተራራማው አገር፥ በቈላውም፥ በዓረባም፥ በቁልቁለቱም፥ በምድረ በዳውም፥ በደቡቡም ያሉ ኬጢያውያን አሞራውያንም ከነዓናውያንም ፌርዛውያንም ኤዊያውያንም ኢያቡሳውያንም የሆኑ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች የመቱአቸው የምድር ነገሥታት እነዚህ ናቸው፥ |
ዲሶን መስፍን፥ ኤሶር መስፍን፥ ሪሶን መስፍን፤ በሴይር ምድር በየሹመታቸው መሳፍንት የሆኑ የሖሪ መሳፍንት እነዚህ ናቸው።
“እግዚአብሔርም እንዳለኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴይርንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን።
ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች ሀገር ታልፋላችሁ፤ እነርሱ ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ።
እስከ ሴይርም ከሚያወጣው ከኤኬል ተራራ ጀምሮ ከአርሞንዔም ተራራ በታች እስከ ሊባኖስ ሜዳና እስከ በላጋድ ድረስ፤ ንጉሦቻቸውን ሁሉ ይዞ መታቸው፤ ገደላቸውም።
እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደ ክፍላቸው በየነገዳቸው ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ የእስራኤል ልጆች ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ።
እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማው በሜዳውም በታላቁ ባሕር ዳር በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥት ሁሉ፥ ኬጤዎናዊዉ፥ አሞሬዎናዊዉም፥ ከነዓናዊዉም፥ ፌርዜዎናዊዉም፥ ኤዌዎናዊዉም፥ ኢያቡሴዎናዊዉም፥ ጌርጌሴዎናዊዉም ይህን በሰሙ ጊዜ፥