Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ ርስት አድ​ርጎ ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለጋ​ድም ልጆች፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ድል አደረጉ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴም ምድራቸውን ለሮቤል፣ ለጋድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የጌታ ባርያ ሙሴና የእስራኤል ልጆች አሸነፉአቸው፤ የጌታም ባርያ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እንግዲህ እነዚህ ሁለት ነገሥታት በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴና በእስራኤል ሕዝብ ጦርነት ድል ሆነው ነበር፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም ይህን ምድር ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና የእስራኤል ልጆች መቱአቸው፥ የእግዚአብሔርም ባሪያ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 12:6
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ንጉሥ በሴ​ዎ​ንና በባ​ሳን ንጉሥ በዐግ ሀገር፥ በጋድ ሀገር፥ የአዴ ልጅ ጌቤር ነበረ፤ በይ​ሁ​ዳም ምድር ላይ እርሱ ብቻ​ውን ሹም ነበረ።


ሙሴም፥ “የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች ሁላ​ቸው የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለጦ​ር​ነት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ቢሻ​ገሩ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ድል ብት​ነሡ ፥ የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ትሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።


የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን ይዘን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ከነ​ዓን ምድር እን​ሻ​ገ​ራ​ለን፤ ከዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ የወ​ረ​ስ​ነው ርስት ይሆ​ን​ል​ናል” አሉት።


ሙሴም ለጋድ ልጆ​ችና ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለዮ​ሴ​ፍም ልጅ ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ፥ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን መን​ግ​ሥት፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን መን​ግ​ሥት፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም፥ ከተ​ራ​ሮ​ችም ጋር ከተ​ሞ​ችን፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ​ትን የም​ድ​ሪ​ቱን ከተ​ሞች ሰጣ​ቸው።


ለሁ​ለቱ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው ነገድ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ርስት አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት ርስ​ታ​ቸው ነውና ለሌዊ ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እድል ፋንታ የላ​ቸ​ውም፤ ጋድም፥ ሮቤ​ልም፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ሥ​ራቅ በኩል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋል።”


አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አሳ​ር​ፎ​አ​ቸ​ዋል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ተመ​ለሱ፤ ወደ ቤታ​ች​ሁና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ሂዱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች