2 ሳሙኤል 22:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፤ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮዎቹ ገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ወደ አምላኬም ጮኽሁ። እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጨነቀኝ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፤ ወደ አምላኬም ጮኽሁ። እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መከራ በደረሰብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም አምላኬን ለመንኩት። በመቅደሱም ሆኖ ድምፄን ሰማ ጩኸቴንም አደመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፥ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኽቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፦ ከአሠሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም ዐውቄአለሁ፤
እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራሮች መሠረት ወረደ፤ ከጥንት ጀምሮ መወርወሪያዎችዋ ወደ ተዘጉ ምድር ወረድሁ፤ አቤቱ ፈጣሪዬ! ሕይወቴ ጥፋት ሳያገኛት ወዳንተ ትውጣ።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነበረበት ጊዜ፥ በታላቅ ጩኸትና እንባ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ጽድቁንም ሰማው።