Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 22:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ፈራ፤ መላ​ል​ሶም ጸለየ፤ ላቡም በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ደም ነጠ​ብ​ጣብ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 እጅግ ተጨንቆም በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም እንደ ደም ነጠብጣብ ወደ ምድር ይፈስስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 በስቃይ ጣር ውስጥ ሆኖ በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም ወደ መሬት እንደሚንጠባጠቡ የደም ጠብታዎች ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ልቡም በጣም ተጨንቆ በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም እንደ ደም ሆኖ ወደ መሬት ይንጠባጠብ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 በፍርሃትም ሲጣጣር አጽንቶ ይጸልይ ነበር፤ ወዙም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 22:44
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ር​ፋቱ ያነ​ጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብታ​ቀ​ርቡ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ረዥም ዕድሜ ያለ​ውን ዘር ታያ​ለች።


ላሜድ። እና​ንተ መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ! በእ​ና​ንተ ዘንድ ምንም የለ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቀ​በት በእኔ ላይ እንደ ተደ​ረ​ገው እንደ እኔ ቍስል የሚ​መ​ስል ቍስል እን​ዳለ ተመ​ል​ከቱ፤ እዩም።


ከሚ​ጸ​ል​ይ​በ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሄደ፤ ከኀ​ዘ​ንም የተ​ነሣ ተኝ​ተው አገ​ኛ​ቸው።


“አሁ​ንስ ነፍሴ ታወ​ከች፤ ግን ምን እላ​ለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍ​ሴን አድ​ናት፤ ነገር ግን ስለ​ዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደር​ሻ​ለሁ።


ለልጁ ስንኳ አል​ራ​ራም፤ ስለ ሁላ​ችን ቤዛ አድ​ርጎ አሳ​ልፎ ሰጠው እንጂ፥ እን​ግ​ዲህ እርሱ ሁሉን እን​ዴት አይ​ሰ​ጠ​ንም?


እር​ሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ፥ በታ​ላቅ ጩኸ​ትና እንባ ከሞት ሊያ​ድ​ነው ወደ​ሚ​ች​ለው ጸሎ​ት​ንና ምል​ጃን አቀ​ረበ፤ ጽድ​ቁ​ንም ሰማው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች