Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 22:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በጨነቀኝ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፤ ወደ አምላኬም ጮኽሁ። እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ወደ አምላኬም ጮኽሁ። እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 መከራ በደረሰብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም አምላኬን ለመንኩት። በመቅደሱም ሆኖ ድምፄን ሰማ ጩኸቴንም አደመጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በጨ​ነ​ቀኝ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠራ​ሁት፤ እን​ዲ​ረ​ዳ​ኝም ወደ አም​ላኬ ጮኽሁ፤ ከመ​ቅ​ደ​ሱም ቃሌን ሰማኝ፤ ጩኸ​ቴም በፊቱ ወደ ጆሮ​ዎቹ ገባ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፥ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኽቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 22:7
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሲኦል ገመዶች ተበተቡኝ፥ የሞት ወጥመዶችም ደረሱብኝ።


የጌታን ስም ጠራሁ፦ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።


ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፥ የምድር መወርወሪያዎችዋ ለዘለዓለም ተዘጉብኝ፤ ጌታ አምላኬ ሆይ አንተ ግን ሕይወቴን ከጉድጓድ አወጣሃት።


የዕርገት መዝሙር። በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኽሁ፥ ሰማኝም።


ጌታም አለ፦ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ በአስገባሪዎቻቸውም ምክንያት የሚጮሁትን ጩኸት ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።


ጌታ ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ምድሪቷ ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።


ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም በፍጹም አያፍርም።


ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥ ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።


እነሆ፥ እርሻችሁን ሲያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ በእናንተ ላይ ይጮኻል፤ የአጫጆቹም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ጆሮ ደርሶአል።


እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤


ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ልብ ጣልኸኝ፥ ወንዝም ከበበኝ፥ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ ላይ አለፉ።


በስቃይ ጣር ውስጥ ሆኖ በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም ወደ መሬት እንደሚንጠባጠቡ የደም ጠብታዎች ሆኑ።


በተጨነቁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች