ንጉሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜምፌቡስቴ የነበረው ሁሉ ለአንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለ።
2 ሳሙኤል 16:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “የጌታህ ልጅ ወዴት ነው?” አለ። ሲባም ንጉሡን፥ “እነሆ፥ የእስራኤል ቤት ዛሬ የአባቴን መንግሥት ይመልስልኛል ብሎ በኢየሩሳሌም ተቀምጦአል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሡ፣ “የጌታህ ልጅ የት ነው?” ሲል ጠየቀው። ሲባም፣ “ ‘የእስራኤል ቤት ዛሬ የአባቴን መንግሥት ይመልስልኛል’ ብሎ ስለሚያስብ፣ በኢየሩሳሌም ተቀምጧል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ንጉሡ፥ “የጌታህ ልጅ የት ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም፥ “ ‘የእስራኤል ቤት ዛሬ የአባቴን መንግሥት ይመልስልኛል’ ብሎ ስለሚያስብ፥ በኢየሩሳሌም ተቀምጦአል” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “የጌታህ የሳኦል የልጅ ልጅ መፊቦሼት የት ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “እስራኤላውያን የአያቱን የሳኦልን መንግሥት መልሰው እንደሚሰጡት ስለ ተማመነ እርሱ አሁን የሚገኘው በኢየሩሳሌም ነው” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ የጌታህ ልጅ ወዴት ነው? አለ። ሲባም ንጉሡን፦ እነሆ፦ የእስራኤል ቤት ዛሬ የአባቴን መንግሥት ይመልስልኛል ብሎ በኢየሩሳሌም ተቀምጦአል አለው። |
ንጉሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜምፌቡስቴ የነበረው ሁሉ ለአንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለ።