Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ንጉ​ሡም ሲባን፥ “ይህ ለአ​ንተ ምን​ድን ነው?” አለው። ሲባም፥ “አህ​ዮቹ የን​ጉሥ ቤተ ሰቦች ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው ዘንድ፥ እን​ጀ​ራ​ውና ተም​ሩም ብላ​ቴ​ኖቹ ይበ​ሉት ዘንድ፥ የወ​ይን ጠጁም በበ​ረሃ የሚ​ደ​ክ​ሙት ይጠ​ጡት ዘንድ ነው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ንጉሡም ሲባን፣ “ይህን ሁሉ ያመጣኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሲባም “አህዮቹን የንጉሡ ቤተ ሰዎች እንዲቀመጡባቸው፣ እንጀራውንና በለሱን ወጣቶቹ እንዲበሉት፣ የወይን ጠጁን ደግሞ በምድረ በዳ የደከሙት እንዲጠጡት ነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ንጉሡም ጺባን፥ “ይህን ያመጣኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “አህዮቹን የንጉሡ ቤተሰቦች እንዲቀመጡባቸው፥ ዳቦውንና ፍራፍሬውን ወጣቶቹ እንዲበሉት፥ የወይን ጠጁን ደግሞ በምድረ በዳ የደከሙት እንዲጠጡት ነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ንጉሥ ዳዊትም “ይህ ሁሉ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “ንጉሥ ሆይ! አህዮቹን ያመጣኋቸው ቤተሰብህ እንዲቀመጡባቸው፥ ዳቦውና ፍራፍሬውም ለተከታዮችህ ስንቅ እንዲሆኑና የወይን ጠጁም በምድረ በዳ በሚደክሙበት ጊዜ እንዲጠጡት ነው” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ንጉሡም ሲባን፦ ይህ ምንድር ነው? አለው። ሲባም፦ አህዮቹ የንጉሥ ቤተ ሰቦች ይቀመጡባቸው ዘንድ፥ እንጀራውና በለሱ ብላቴኖቹ ይበሉት ዘንድ፥ የወይን ጠጅም በበረሀ የሚደክሙት ይጠጡት ዘንድ ነው አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 16:2
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ማርና ቅቤ፥ በግና ላም ይበሉ ዘንድ ለዳ​ዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር ላሉ ሰዎች አመጡ። ሕዝቡ በም​ድረ በዳ ተር​በ​ውና ተጠ​ም​ተው ደክ​መው ነበ​ርና።


በሠ​ላሳ ሁለት የአ​ህያ ግል​ገ​ሎች ይቀ​መጡ የነ​በሩ ሠላሳ ሁለት ልጆ​ችም ነበ​ሩት፤ ለእ​ነ​ር​ሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች የተ​ባሉ በገ​ለ​ዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተ​ሞች ነበ​ሩ​አ​ቸው።


በነ​ጫጭ አህ​ዮች ላይ የም​ት​ጫኑ፥ በፍ​ርድ ወን​በር ላይ​የ​ም​ት​ቀ​መጡ፥ በመ​ን​ገ​ድም የም​ት​ሄዱ በቃ​ላ​ችሁ ተና​ገሩ።


የሕ​ዝ​ብ​ህም ልጆች፦ ይህ የም​ታ​ደ​ር​ገው ነገር ምን ማለት እንደ ሆነ አት​ነ​ግ​ረ​ን​ምን? ብለው በተ​ና​ገ​ሩህ ጊዜ፥ አንተ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም አለ፥ “ጌታዬ፥ ንጉሥ፥ አገ​ል​ጋዬ አታ​ለ​ለኝ፥ እኔ ባሪ​ያህ አን​ካሳ ነኝና፦ ከን​ጉሡ ጋር እሄድ ዘንድ አህ​ያ​ዬን ጫን​ልኝ፤ እኔም እቀ​መ​ጥ​በ​ታ​ለሁ አል​ሁት።


ሀገ​ሪ​ቱም ሁላ በታ​ላቅ ድምፅ አለ​ቀ​ሰች። ሕዝ​ቡም ሁሉ በቄ​ድ​ሮን ወንዝ ተሻ​ገሩ፤ ንጉ​ሡም ደግሞ የቄ​ድ​ሮ​ንን ወንዝ ተሻ​ገረ፤ ንጉ​ሡና ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተሻ​ገሩ።


ከዚ​ህም በኋላ አቤ​ሴ​ሎም ሰረ​ገ​ላና ፈረ​ሶች፥ በፊ​ቱም የሚ​ሮጡ አምሳ ሰዎች አዘ​ጋጀ።


አሁ​ንም ባሪ​ያህ ወደ ጌታዬ ያመ​ጣ​ች​ውን ይህን መተ​ያያ ተቀ​በል፤ በጌ​ታ​ዬም ዘንድ ለሚ​ቆሙ ሰዎች ስጣ​ቸው።


ከሕ​ዝ​ቡም አንድ ሰው መልሶ፥ “አባ​ትህ፦ ዛሬ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝ​ቡን መሐላ አም​ሎ​አ​ቸ​ዋል” አለው፤ ሕዝ​ቡም ደከሙ።


ዔሳ​ውም፥ “ያገ​ኘ​ሁት ይህ ሠራ​ዊት ሁሉ ምንህ ነው?” አለ። እር​ሱም፥ “በጌ​ታዬ ፊት ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ ነው” አለ።


አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን፥ “ለብ​ቻ​ቸው ያቆ​ም​ሃ​ቸው እነ​ዚያ ሰባ ቄቦች በጎች ምን​ድን ናቸው?” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች