Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 88 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው የኤ​ታን ትም​ህ​ርት።

1 አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም እዘ​ም​ራ​ለሁ። ጽድ​ቅ​ህ​ንም በአፌ ለልጅ ልጅ እና​ገ​ራ​ለሁ።

2 “ምሕ​ረ​ትን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አን​ጻ​ለሁ” ብለ​ሃ​ልና፥ ጽድ​ቅህ በሰ​ማይ ጸና።

3 ከመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግሁ፥ ለባ​ሪ​ያ​ዬም ለዳ​ዊት ማልሁ፥

4 ዘር​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ፥ ዙፋ​ን​ህ​ንም ለልጅ ልጅ አጸ​ና​ለሁ።

5 አቤቱ፥ ሰማ​ያት ክብ​ር​ህን ጽድ​ቅ​ህ​ንም ደግሞ በቅ​ዱ​ሳን ማኅ​በር ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደ​መ​ናት ማን ይተ​ካ​ከ​ለ​ዋል? ከአ​ማ​ል​ክ​ትስ ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማን ይመ​ስ​ለ​ዋል?

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ዱ​ሳን ምክር ክቡር ነው፤ በዙ​ሪ​ያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላ​ቅና ግሩም ነው።

8 አቤቱ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አቤቱ፥ አንተ ብርቱ ነህ፥ እው​ነ​ትም ይከ​ብ​ብ​ሃል።

9 የባ​ሕ​ርን ኀይል አንተ ትገ​ዛ​ለህ፥ የሞ​ገ​ዱ​ንም መና​ወጥ አንተ ዝም ታሰ​ኘ​ዋ​ለህ።

10 አንተ ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውን እንደ ተገ​ደለ አዋ​ረ​ድ​ኸው፥ በኀ​ይ​ል​ህም ክንድ ጠላ​ቶ​ች​ህን በተ​ን​ሃ​ቸው።

11 ሰማ​ያት የአ​ንተ ናቸው፥ ምድ​ርም የአ​ንተ ናት፤ ዓለ​ምን በሙሉ አንተ መሠ​ረ​ትህ።

12 ባሕ​ር​ንና መስ​ዕን አንተ ፈጠ​ርህ፤ ታቦ​ርና አር​ሞ​ን​ኤም በስ​ምህ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ስም​ህ​ንም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።

13 ክን​ድህ ከኀ​ይ​ልህ ጋር ነው፤ እጅህ በረ​ታች፥ ቀኝ​ህም ከፍ ከፍ አለች።

14 የዙ​ፋ​ንህ መሠ​ረት ፍት​ሕና ርትዕ ነው፤ ምሕ​ረ​ትና እው​ነት በፊ​ትህ ይሄ​ዳሉ።

15 እል​ል​ታን የሚ​ያ​ውቅ ሕዝብ ብፁዕ ነው፤ አቤቱ፥ በፊ​ትህ ብር​ሃን ይሄ​ዳሉ።

16 በስ​ምህ ቀኑን ሁሉ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም ከፍ ከፍ ይላሉ፤

17 የኀ​ይ​ላ​ቸው ትም​ክ​ሕት አንተ ነህና፥ በይ​ቅ​ር​ታ​ህም ቀን​ዳ​ችን ከፍ ከፍ ይላ​ልና።

18 ረድ​ኤ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። ንጉ​ሣ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነውና።

19 በዚያ ጊዜ ለል​ጆ​ችህ በራ​እይ ተና​ገ​ርህ፥ እን​ዲ​ህም አልህ፥ “ረድ​ኤ​ትን በኀ​ይል ላይ አኖ​ርሁ፤ ከሕ​ዝቤ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትን ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግሁ።

20 ባሪ​ያ​ዬን ዳዊ​ትን አገ​ኘ​ሁት፥ የተ​ቀ​ደሰ ዘይ​ት​ንም ቀባ​ሁት።

21 እጄም ትረ​ዳ​ዋ​ለች፥ ክን​ዴም ታጸ​ና​ዋ​ለች፥

22 ጠላት በእ​ርሱ ላይ አይ​ጠ​ቀ​ምም፥ የዐ​መፃ ልጅም መከራ አይ​ጨ​ም​ር​በ​ትም።

23 ጠላ​ቶ​ቹን ከፊቱ አጠ​ፋ​ለሁ፥ የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም አዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።

24 እው​ነ​ቴና ምሕ​ረ​ቴም ከእ​ርሱ ጋር ነው፥ በስ​ሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።

25 እጁን በባ​ሕር ላይ ቀኙ​ንም በወ​ን​ዞች ላይ አኖ​ራ​ለሁ።

26 እርሱ “አባቴ አንተ ነህ፥ አም​ላኬ ረዳ​ቴና መድ​ኃ​ኒ​ቴም ነህ” ይላል።

27 እኔም ደግሞ በኵሬ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፥ ከም​ድር ነገ​ሥ​ታ​ትም ከፍ ይላል።

28 ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይቅ​ር​ታ​ዬን ለእ​ርሱ እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፥ ለኪ​ዳ​ኔም እርሱ የታ​መነ ነው።

29 ዘሩ​ንም ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ዙፋ​ኑ​ንም እንደ ሰማይ ዘመን አደ​ር​ጋ​ለሁ።

30 “ልጆቹ ግን ሕጌን ቢተዉ፥ በፍ​ር​ዴም ባይ​ሄዱ፤

31 ሥር​ዐ​ቴ​ንም ቢያ​ረ​ክሱ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ባይ​ጠ​ብቁ፤

32 ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን በበ​ትር፥ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም በመ​ቅ​ሠ​ፍት እጐ​በ​ኛ​ታ​ለሁ።

33 ይቅ​ር​ታ​ዬን ግን ከእ​ርሱ አላ​ር​ቅም፥ በእ​ው​ነ​ቴም አል​በ​ድ​ልም፤

34 ኪዳ​ኔ​ንም አላ​ረ​ክ​ስም፥ ከአ​ፌም የወ​ጣ​ውን አል​ለ​ው​ጥም።

35 ዳዊ​ትን እን​ዳ​ል​ዋ​ሸው አንድ ጊዜ በቅ​ዱ​ስ​ነቴ ማልሁ።

36 ዘሩ ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥ ዙፋ​ኑም በፊቴ እንደ ፀሐይ ይኖ​ራል።

37 ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ጨረቃ ይጸ​ናል። ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም በሰ​ማይ የታ​መነ ነው።”

38 አንተ ግን ናቅ​ኸው፥ ጣል​ኸ​ውም፥ የቀ​ባ​ኸ​ው​ንም አቃ​ለ​ል​ኸው።

39 የባ​ሪ​ያ​ህ​ንም ኪዳን አፈ​ረ​ስህ፥ መቅ​ደ​ሱ​ንም በም​ድር አረ​ከ​ስህ።

40 ቅጥ​ሩን ሁሉ አፈ​ራ​ረ​ስህ፥ አም​ባ​ዎ​ቹ​ንም የሚ​ያ​ስ​ፈሩ አደ​ረ​ግህ።

41 መን​ገድ አላ​ፊም ሁሉ ተና​ጠ​ቀው፥ ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቹም ስድብ ሆነ።

42 የጠ​ላ​ቶ​ቹ​ንም ቀኝ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግህ። ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ሁሉ ደስ አሰ​ኘህ።

43 የሰ​ይ​ፉ​ንም ረድ​ኤት መለ​ስህ፥ በሰ​ል​ፍም ውስጥ አል​ደ​ገ​ፍ​ኸ​ውም።

44 ከን​ጽ​ሕ​ና​ውም ሻር​ኸው፥ ዙፋ​ኑ​ንም በም​ድር ጣልህ።

45 የዙ​ፋ​ኑ​ንም ዘመን አሣ​ነ​ስህ፥ በላ​ዩም እፍ​ረ​ትን ጨመ​ርህ።

46 አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ፊት​ህን ትመ​ል​ሳ​ለህ? እስከ መቼስ ቍጣህ እንደ እሳት ይነ​ድ​ዳል?

47 ኀይሌ ምን እንደ ሆነ ዐስብ፤ በውኑ የሰ​ውን ልጅ ሁሉ ለከ​ንቱ ፈጠ​ር​ኸ​ውን?

48 ሕያው ሆኖ የሚ​ኖር፥ ሞት​ንስ የማ​ያይ ሰው ማን ነው? ነፍ​ሱ​ንስ ከሲ​ኦል እጅ የሚ​ያ​ድ​ናት ማን ነው?

49 አቤቱ፥ የቀ​ድሞ ይቅ​ር​ታህ ወዴት ነው? ለባ​ሪ​ያህ ለዳ​ዊት በእ​ው​ነት የማ​ልህ፥

50 አቤቱ፦ ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን የሰ​ደ​ቡ​አ​ቸ​ውን ስድብ፥ በብ​ብቴ ብዙ አሕ​ዛ​ብን የተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትን፥

51 አቤቱ፥ ጠላ​ቶ​ችህ የሰ​ደ​ቡ​ትን የቀ​ባ​ኸ​ውን ዘመን የሰ​ደ​ቡ​ትን ስድብ ዐስብ።

52 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ስ​ገን። ይሁን ይሁን።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች