መዝሙር 83:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በጸጥታ አትቆይ፥ አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ፣ ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ ጠላቶችህ ዐምፀዋል፤ የሚጠሉህ ሁሉ ራሳቸውን በአንተ ላይ አንሥተዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ነፍሴ አደባባዮችህን በመውደድ ደስ አላት፤ ልቤም ሥጋዬም በሕያው እግዚአብሔር ደስ አላቸው። |
የተገዳደርኸው የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደርግህበት፥ ዓይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን!’
ጲላጦስም ይህ ነገር ሁከት ከማስነሳት በስተቀር ምንም እንደማይጠቅም ባየ ጊዜ፥ ውሃ ወስዶ “እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ ጉዳዩ የእናንተ ነው፤” ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።
አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፤ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤
እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፥ “እነደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፤ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና፤” አሉ።
ስለዚህ ምድያማውያን በእስራኤላውያን ተሸነፉ፤ ዳግመኛም ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም። ጌዴዎን በሕይወት እስካለ ጊዜ ድረስ ምድሪቱ አርባ ዓመት ሰላም አገኘች።