Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 83:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እነሆ፥ ጠላቶችህ ዐምፀዋል፤ የሚጠሉህ ሁሉ ራሳቸውን በአንተ ላይ አንሥተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ፣ ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አቤቱ፥ በጸጥታ አትቆይ፥ አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አቤቱ፥ ነፍሴ አደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ህን በመ​ው​ደድ ደስ አላት፤ ልቤም ሥጋ​ዬም በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 83:2
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔን የሚጠሉ ሁሉ በፍርሃት በእግሬ ሥር ይደፋሉ፤ ቅጣታቸውም ለዘለዓለም ይጸናል።


ስለዚህ ጲላጦስ ይህ ነገር ሁከት እንደሚያስነሣ እንጂ ሌላ ምንም እንደማይጠቅም ባየ ጊዜ ውሃ አስመጥቶ “እኔ ለዚህ ሰው ሞት ኀላፊ አይደለሁም፤ ኀላፊነቱ የእናንተ ነው!” ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።


እንደ ባሕር ሞገድ ድምፀ ለሚያሰሙ ለብዙ ወገን ስብስቦች ወዮላቸው! እንደ ኀይለኛ ጐርፍ ለሚጣደፉ ሕዝቦች ወዮላቸው!


በዚህ ዐይነት ምድያም በእስራኤላውያን ተሸነፈች፤ ዳግመኛም ለእስራኤላውያን የምታሰጋ አልሆነችም፤ ጌዴዎን እስከ ሞተም ድረስ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።


ጠቡ እየከረረ ስለ ሄደ ሰዎቹ ጳውሎስን እንዳይቦጫጭቁት ፈርቶ አዛዡ “ውረዱና ጳውሎስን ከሰዎቹ መካከል ነጥቃችሁ አምጡ! ወደ ጦሩ ሰፈርም ውሰዱት!” በማለት ወታደሮቹን አዘዘ።


እስከዚህ ድረስ ሕዝቡ ሁሉ የጳውሎስን ንግግር ያዳምጡ ነበር፤ ከዚህ በኋላ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፦ “እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከምድር ላይ ይወገድ! እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት መኖር አይገባውም!” እያሉ ጮኹ።


ከተማዋ በሙሉ ታወከች፤ ሕዝቡም ሁሉ እየሮጡ በአንድነት መጡና ጳውሎስን ይዘው እየጐተቱ ከቤተ መቅደስ አወጡት፤ የቤተ መቅደሱ በሮችም ወዲያውኑ ተዘጉ።


አይሁድ ግን ቀንተው የሚበጠብጡ ሥራ ፈቶችን ከየመንገዱ ሰበሰቡና አሳደሙ። በከተማው ውስጥ ብጥብጥ እንዲነሣ አደረጉ፤ ጳውሎስንና ሲላስን አውጥተው ለሕዝቡ ለመስጠትም የኢያሶንን ቤት ከበቡ።


ሕዝቡም ሁሉ ተባብሮ በእነርሱ ላይ ተነሣ። ባለሥልጣኖችም የጳውሎስንና የሲላስን ልብስ ገፈፉና በዱላ እንዲደበደቡ አዘዙ።


በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”


ዐይንህን በትዕቢት አቅንተህ፥ ድምፅህን ከፍ አድርገህ በመጮኽ የተዳፈርከውና የተሳደብከው ማንን ይመስልሃል? የእስራኤልን ቅዱስ አይደለምን?’


እግዚአብሔር ሆይ! ባሕሮች ይነሣሉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ የሞገዳቸውም ድምፅ ይሰማል።


ጠላቶችህ ዘወትር የሚጮኹትን ጩኸትና የሚደነፉትን ድንፋታ አስታውስ።


ጠላቶችህ “ድል አደረግን” ብለው በቤተ መቅደስህ ውስጥ ይደነፋሉ፤ በዚያም የድል ምልክት የሆነውን ዐርማቸውን ተክለዋል።


በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”


የማመሰግንህ አምላክ ሆይ፥ እባክህ ዝም አትበል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች